የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በተወሰኑ የአማራ አካባቢዎች ላይ ትንኮሳ ጀምሯል ሲል ዛሬ የአማራ ክልል ባወጣው መግለጫ ተናገረ፡፡
ከቀናት በፊት የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የአማራ ክልል በተማሪዎች የመማሪያ መፅሐፍት የትግራይ ክልልን ቦታዎች የራሱ አስመስሎ በካርታው በማካተት እያስተማረበት ነው ሲል መክሰሱ ይታወሳል፡፡
በዚሁ መግለጫው የአማራ ክልል ማስተካከያ የማያደርግ ከሆነ ለሚፈጠረው ችግር ሀላፊነቱን ይወስዳል ማለቱም ይታወሳል፡፡
የአማራ ክልል በበኩሉ ጊዜአዊ አስተዳደሩ የመማሪያ መፅሐፍትን በማጣቀስ ያወጣው መግለጫ ዛቻና ፀብ አጫሪነት ሲል ገልጾታል፡፡
በተጨማሪም ወደ አማራ ክልል ካርታ ተካቷል ያላቸውን ስፍራዎች የሚገኙ ህዝቦችን ታሪካዊ እውነታና ተጨባጭ ማስረጃዎችን እንዲሁም ነባራዊ አቅን የካደ አሳሳች መግለጫ ሲልም ገልፆታል፡፡
ሁለቱ ክልሎች በይገባኛል የሚወዛገቡባቸው ቦታዎች መኖራቸው የሚታወቅ ነው፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments