መጋቢት 2፣2016 - በኢትዮጵያ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ምርቶቻቸውን ወደ ሩሲያ እንዲልኩ ከስምምነት መደረሱ ተነገረ
- sheger1021fm
- Mar 11, 2024
- 1 min read
በኢትዮጵያ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ምርቶቻቸውን ወደ ሩሲያ ገበያ እንዲልኩ ከስምምነት መደረሱ ተነገረ።
ለኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ምርቶች በሩስያ ሰፊ ገበያ እንዳለ በጥናት ተረጋግጧል ተብሏል።
ይህንን በጥናት አረጋግጠናል ሲሉ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘመን ጁነዲ ነግረውናል።
ይህንን ገበያ ለመጠቀም የሚስችል ስምምነት ዛሬ የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አክሊሉ ታደሰ እና በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጌኒ ተርኪሂን በመከሩበት ወቅት መደረሱንም አክለዋል
የሩሲያን ገበያ ከመጠቀም ባሻገር የሀገሪቱ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው እንዲሰሩ ሰፊ የማግባባት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ ዘመን ነግረውናል።
በድሬደዋ ፣ ሃዋሳና ጅማ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ገብተው ለመስራት የተስማሙ የሀገሪቱ ባለሃብቶች፤ አሁን ላይ ስራ ለመጀመር በመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛሉ ብለውናል።
በነበረው ውይይት ኢንቨስትመንት ነክ ከሆኑ ጉዳዮች ባሻገር፤ የኢንዱሰትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ሰራተኞችን አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ የተለያዩ ስልጠናዎችን በሩሲያ በኩል ለማመቻቸት ስምምነት መደረሱ ተነግሯል።
ንጋቱ ረጋሣ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Комментарии