top of page

መጋቢት 20 2017 - የፋሲካ ኤክስፖ የፊታችን ማክሰኞ በይፋ እንደሚከፈት ተነገረ

ታሜሶል ኮሚኒኬሽን ያዘጋጀው #የፋሲካ_ኤክስፖ የፊታችን ማክሰኞ በይፋ እንደሚከፈት ተነገረ።


ኤክስፖው "ቴሌ ብር አዲስ ነገር እስከ ፋሲካ 2017 ኤክስፖ" የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።


በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል አስከ ሚያዚያ 11/2017 የሚካሄደው ኤክስፖው ታሜሶል ኮሚኒኬሽን፣ ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን እና ከሊያን ቢዝነስ ግሩኘ ጋር በመሆን አዘጋጅተውታል።

ኤክስፖው ከዚህ ቀደም ከተደረጉ የንግድ ትርኢቶች የተለየ እና ልዩ የሚያደርጉት በርካታ ዝግጅቶች ማቀዱን ተነግሯል።


በቴሌ ብር አዲስ ነገር እስከ ፋሲካ ኤክስፖ ላይ ከ300 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ንግድ ተቋማት ምርት እና አገልግሎቶቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል።


ከንግድ ተቋማት በተጨማሪ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና በልዩ ትኩረት ለአካል ጉዳተኞች እድል፣ በአካል ጉዳተኞች የተመረቱ ምርቶች ለሽያጭ ይቀርባሉ ተብሏል።


በግብይት ወቅት በቴሌብር ለሚከፍሉ 10 በመቶ ተመላሽ እንደሚያገኙም ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ላይ ተነግሯል።


ወደ ኤክስፖ ለሚመጡ ጎብኚዎች የተለያዩ የፆም ምግቦች(በብፌ መልክ) በአንድ ቦታ ተዘጋጅቷል ተብሏል።


በኤክስፖው ላይ አንድ የቤት መኪና፣ የሞባይል ቀፎ፣ ሞተር ሳይክል በሽልማት መልክ እንደሚወጡ ተነግሯል።


ታሜሶል ኮሚኒኬሽን የፋሲካ በዓል ዋዜማ ኤክስፖ ጨረታ ያሸነፈው በ60 ሚሊየን ብር ነው መባሉ ይታወሳል።


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page