top of page

መጋቢት 24፣ 2016 - የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ሰዎች ፎቶግራፍ አውጥቷል

  • sheger1021fm
  • Apr 2, 2024
  • 1 min read

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ሰዎች ፎቶግራፍ አወጣ።


ግለሰቦቹ ከ 305,000 ብር እስከ 108,000 ብር የወሰዱ መሆናቸው ተናግሯል።


በባንኩ የሲስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6፣2016 ዓ/ም ያለአግባብ ከባንኩ የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ እስከ መጋቢት 2፣2016 ዓ/ም በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ መሠረት 10,857 ግለሰቦች ያለባቸውን ገንዘብ አጠናቀው መልሰዋል ተብሏል፡፡


ነገር ግን የተሰጠውን ተደጋጋሚ እድል ተጠቅመው ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦች እንዳሉ ባንኩ አስረድቷል።


እስካሁን ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን የመጀመሪያ ዙር ፎቶግራፍ በባንኩ ድረ-ገጽ እና የማህበራዊ ትስስር ገፆች ለማውጣት  ተገድጃለሁ ብሏል።


የገንዘብ መመለሻ ጊዜውን ለመጨረሻ ጊዜ እስከ መጋቢት 25፣2016 ዓ/ም ያራዘመው ባንኩ  ይህን የመጭረሻ እድል ተጠቅመው ገንዘቡን እንዲመልሱ አሳስቧል።


በተሰጠው የጊዜ ገደብ የማይመልሱትን ወደ ህግ አቀርባለሁ ሲልም አስጠንቅቋ።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page