top of page

መጋቢት 24 2017 - በትናንቱ የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ ዶላር በ4 ብር ያህል ቅናሽ ባለው ብር መሸጡ የብርን የመግዛት አቅም እንዲበረታ ያደርገዋል ተባለ

  • sheger1021fm
  • 20 hours ago
  • 1 min read

በትናንቱ የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንድ ዶላር በ4 ብር ያህል ቅናሽ ባለው ብር መሸጡ የብርን የመግዛት አቅም እንዲበረታ ያደርገዋል ተባለ፡፡


በጨረታው አንድ ዶላር በአማካይ በ131 ነጥብ 7 ብር ተሸጧል፡፡


ይህም ከወር በፊት ከነበረው ጨረታ ከተሸጠበት አማካይ ዋጋ በ4 ብር ያህል ያነሰ ነው፡፡


ይህም የብርን የመግዛት አቀቅም ከፍ እንደሚያደርገው በጉዳዩ ላይ ሸገር ያነጋገራቸው የፋይናንስና የኢንቨስትመንት ባለሙያው አቶ መርዕድ ፍቅረ ዮሐንስ ነግረውናል፡፡


ብሔራዊ ባንክ በየሁለት ሳምንቱ የዶላር ጨረታ አቀርባለሁ ማለቱም ለብር የመግዘት አቅም በጎ ጎን እንደሚኖረው አክለዋል፡፡


በትናንቱ ጨረታ የተሳተፉ ባንኮች ቁጥር ደግሞ ካለፈው ጨረታ በ15 ያነሰ ሲሆን ይህም ባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንዳለባቸው የሚያሳይ መሆኑን ባለሞው ጠቅሰዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው




Komentar


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page