መጋቢት 25 2017 - የትምህርት ሚኒስቴር ከሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን የመምህራን ባንክ ለማቋቋም እየተሰራ ነው አለ
- sheger1021fm
- 21 hours ago
- 1 min read
የትምህርት ሚኒስቴር በሃገር አቀፍ ደርጃ ያለውን የመምህራን ችግር ለመፍታት የሶስተኛ ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት ያክል እንዲያስተምሩ ሊደርግ እንድሆነም ተናግሯል።
ይህን የተናገሩት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብረሃኑ ነጋ ናቸው።
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብረሃኑ ነጋ ይህን የተናገሩት ባለፉት ዓመታት በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፍተና ላይ ለተስተዋለው የውጤት ውድቀት መንስኤ ምን እንደሆነ ለማወቅ የተጠና ጥናት ለውይይት በቀርበበት መድረክ ላይ ነው።
በቀርበው ጥናት መሠርት ለውጤት መታጣቱ የመምህራን አቅም ማነስ፣ የ10ኛ ክፍል ፍተና መቅረት ፣ የትምህርት ግብዓቶች አለመሟላት እና የመሰረተ ልማት ጉድለት ከበዙት ምክንያቶች ጥቂቶቹ ናችው ተብሏል።

ጥናቱ የቀረበው በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለሰው ሃይል ስራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮቾ ቋሚ ኮሚቴ ሲሆን በውይይቱ ላይም ከምክር ቤቱ አባላት በተጨማሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
በውይይቱ ላያ መምህራንን በተመለክተ ሃሳብ የሰጡት ከፍኔ ኢፋ (ዶ/ር) የተባሉ የምክር ቤት አባል በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ውጤት ያለው ህክምና ፣ ኢንጂነሪንግ ውይም ሌላ ነገር ነው የሚመደበው የመጨረሻ ውጤት ካመጣ ግን እየግፋን እየውሰድን አስተማሪ እንዲሆን እናደርጋለን ከእንድዚህ አይነት መምህር ምን ይጠብቃል ሲሉ ጠይቀዋል።
የመምህራን የኑሮ ሁኔታን ማሻሻልም በአገር አቀፍ ደረጃ ለጠፋው የትምህርት ውጤት እንዱ ምክንያት ነው ተብሏል።
ይህን ለማሻሻል ደግሞ የመምህራን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ያስፈልጋል ተብሏል።
የመምህራንን የኑሮ ሁኔታ በተመለከተ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብረሃኑ ነጋ ባደርጉት ንግግር የመምህራን ባንክ ለመጅመር እንቀስቃሴ እየተደርግ ነው ብለዋል።
እስከሚቀጥለው ዓመትም ይቋቋማል በዬ ተስፋ አደርጋለሁ ሲሉ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ይህም የመምህራንን ችግር ይፍታል ብለን ሳይሆን በአንስተኛ ወለድ ቤት ለመስራት ከሚያስችላቸው የፋይናንስ ስራዓቱ ጋር እንዲተሳሰርላቸው ነው ብለዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ በአገር አቀፍ ድርጃ የመምህራን እጥርት እንዳለ ተናግረዋል።
በቅርቡ በተሰራ የዳሰሳ ጥናትም 100 ሺህ የሚሆን የመምህራን እጥረት አለ ብለዋል።
ይህንንም ለመፈታተን ከተቻለ በአለንበት ዓመት ካልሆነ በመጪው ዓመት የ3ኛ ዓመት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎቸ ለእንድ ዓመት ያክል ከምረቃችው ብፊት እንዲያስተምሩ ለማድርግ እየተሰራ እንደሆነ ተናግርዋል።
ያሬድ እንዳሻው
Comments