top of page

መጋቢት 25፣2016 - ኢትዮጵያ እና ፑንትላንድ ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶችን ለማሻሻል መስማማታቸው ተነገረ

  • sheger1021fm
  • Apr 3, 2024
  • 1 min read

ኢትዮጵያ እና  የሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት አካል ሆና የቆየችው ፑንትላንድ ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶችን ለማሻሻል መስማማታቸው ተነገረ፡፡

 

ፑንትላንድ ከእንግዲህ ከሞቃዲሾ ጋር ያለኝን ማንኛውንም ዓይነት ግንኙነት አቋርጫለሁ ማለቷ ይታወሳል፡፡

 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ  አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፤ በፑንትላንድ የገንዘብ ሚኒስትር  መሀመድ ፋራህ መሀመድ የተመራ ከፍተኛ የሚኒስትሮች ልዑካን ቡድንን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

 

አዲስ የተመረጠው የፑንትላንድ መንግስት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ፍላጎት እንዳለው አስረድቷል ተብሏል።

 

በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በኢነርጂ እና በመሠረተ ልማት መስክ ለሚኖር ትብብር ትኩረት እንደሚሰጥ ተጠቅሷል።

 

ኢትዮጵያ በተለይ በጸጥታና በትምህርት ዘርፍ ለፑንትላንድ እያደረገች ላለው ድጋፍ ልዑካን ቡድኑ ምስጋና አቅርቧል።

ኢትዮጵያ ከፑንትላንድ ጋር ያላት ግንኙነት እንዲጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ለሚኖራት ግንኙነት ቁርጠኛ መሆኗን አምባሳደር ምስጋኑ ተናግረዋል።

 

የፑንትላንድ አስተዳደር ከእንግዲህ ከሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት ጋር አንዳችም ግንኙነት አይኖረኝም ያለው የፌዴራሉ ምክር ቤት ህገ መንግስታዊ ማሻሻያ ማድረጉን ተከትሎ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

 

ለፌዴራል መንግስቱ እውቅና የነፈገው የፑንትላንድ አስተዳደር ከእንገዲህ ራሴን የቻልኩ ነፃ መንግስት ነኝ ማለቱ ተሰምቷል፡፡

 

ንጋቱ ሙሉ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1

 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page