በመሬት ልማትና አስተዳደር በተጠናው የመዋቅር ጥናት የሰራተኞች ድልድል ተካሂዶ ምደባ እስከሚካሄድ ድረስ ከጥር 21/2016 ዓ.ም ጀምሮ የመሬት አገልግሎት ታግዶ መቆየቱ ይታወሳል።
አጠቃላይ የሰራተኛ ድልድሉ በመጠናቀቁ ከመጋቢት 23፣2016 ዓ/ም ጀምሮ የመሬት አገልግሎት መጀመሩን የከተማዋ መሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ተናግሯል።
የመሬት እግድ አልግሎቱ መነሳቱን በተመለከተም የቢሮው ሃላፊ አቶ ሲሳይ ጌታቸው ለሁሉም ከፍለ ከተሞች በላኩት ደብዳቤ አስረድተዋል።
ቢሮው ከዚህ በፊት የነበረውን ብልሹ አሰራር ለማስቀረት ሲባል አዲስ ሥርዓት ዘርግቶ፤ የመሬት ይዞታ አገልግሎት መዝገቦች ሁሉ ዲጂታል አድርጌአለሁ ማለቱ አይዘነጋም፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
ShegerFM: @ShegerFMRadio102_1
Comments