መጋቢት 25 2017 - ከ10 ዓመት በኋላ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ተመራጭ ከሆኑ የቱሪዝም መዳረሻ ሃገራት አንዷ ለማድረግ አዲሱ ረቂቅ የቱሪዝም ፖሊሲ ውጥን መያዙን ተነገር
- sheger1021fm
- 19 hours ago
- 2 min read
ከ10 ዓመት በኋላ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ተመራጭ ከሆኑ የቱሪዝም መዳረሻ ሃገራት አንዷ ለማድረግ አዲሱ ረቂቅ የቱሪዝም ፖሊሲ ውጥን መያዙን ተነገር።
የቱሪዝም ረቂቅ ፖሊሲ አሁን በዘርፉ ያሉ አለም ዓቀፋዊ ለውጦች ጋር እንዲግባባ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው ሲባል ሰምተናል።
የቱሪዝም ሚኒስቴር በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ይመለከታቸዋል ካላቸው ጋር ውይይት እያደረገ ነው።
ከዚህ ቀደም የነበረው የቱሪዝም ልማት ፖሊሲ አሁን ላይ ካለው የቱሪዝም እንቅስቃሴ ጋር ተወዳዳሪ ሆኖ ለማስቀጠል ብቁ አይደለም ተብሏል።
የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሣ በረቂቅ ደረጃ ላይ ያለው የቱሪዝም ፖሊሲ መንግስት በዘርፉ እየሰራቸው ካሉ አሁናዊ ስራዎችን የሚደግፍ ነው ብለዋል፡፡

ቱሪዝም 5ተኛ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ምሰሶ ተደርጓል፣ ዘርፉ የሚመራበትም ፖሊሲ ከዚህ ጋር አንዲሄድ በማስፈለጉ ማሻሻያ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
አሁን ላይ ለቱሪዝም ዘርፍ ዋንኛ የፋይናንስ አማራጭ ልማት ባንክ ነው ነገር ግን ዘርፉ እንዲያድግ ሌሎች የፋይናንስ አማራጮችን ማየትና ቱሪዝሙን በሚገባ ማስተዋወቅ ረቂቅ ፖሊሲው አትኩሮት ሰጥቶታል።
የቱሪዝም ልማት ፈንድ ማቋቋም አንዱ እቅድ መሆኑንም ሰምተናል።
በተለይም የቱሪዝም የአንድ ሰሞን ብቻ አንዳይሆን ዓመቱን ሙሉ የቱሪስት ፍሰት እንዲኖር ዘርፉን ማስተዋወቅ፣ የተለያዩ ቱሪዝም ነክ ኩነቶች ማዘጋጀት እንዲሚገባ በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ተጠቅሷል፡፡
አሁን ላይ ቱሪዝምን ለማስኬድና ለማሳደግ ቀጣናዊ ትስስር ማድረግን ይጠይቃል የተባለ ሲሆን ረቂቅ ፖሊሲው ይህንን በሚገባ እንዲመልስ ያደርጋል መባሉን ሰምተናል።
የቱሪዝም ዘርፍ ቴክኖሎጂን ከመጠቀም ፣ መረጃ በሚገባ አደራጅቶ ከመያዝ አኳያ ክፍተቶች አሉ ተብሏል።
አዲሱ ፖሊሲ እነዚህ ክፍተቶች መሙላት የሚቻልበት መላ ይዟል ተብሏል።
እስከ 2012 ባለው መረጃ መሰረት የቱሪዝም ዘርፍ በየአመቱ 2.7 በመቶ ቀጥታ ለሃገራዊ ጥቅል እድገት አስተዋፅኦ ያደርጋል የተባለ ሲሆን ይህንን ማሳደግ እንደሚያስፈልግም ተነግሯል።
የቪዛ አሰጣጥ አገልግሎት ማሻሻል፣ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ማሳደግ ፣ አግልግሎት ሰጪ ተቋማት ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማብቃት ትኩረት ያገኙ ጉዳዮች ናቸው ተብሏል።
ፖሊሲው ከኢትዮጵያ የተዘረፉና በሌሎች ሃገራት እጅ ያሉ ቅርሶች በኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንፀላዎች በኩል ማስመለስ የሚቻልበን መንገድ አስቀምጧል።
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comments