top of page

መጋቢት 25 2017 - የንግድ ስራ የሚመራበት ደንብ ቢኖርም እስካሁን በአግባቡ የሚመራበት ወጥ የሆነ ፖሊሲ አልነበረውም ተባለ

  • sheger1021fm
  • 1 day ago
  • 1 min read

የንግድ ስራ የሚመራበት ደንብ ቢኖርም እስካሁን በአግባቡ የሚመራበት ወጥ የሆነ ፖሊሲ አልነበረውም ተባለ፡፡


ይህ የተባለው ዛሬ በኢትዮጵያ የንግድ ፖሊሲ ረቂቅ ላይ ውይይት እየተካሄደ ባለበት ወቅት ነው፡፡


የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ ሀገሪቱ እስካሁን የንግድ ሥርዓትን የሚሰራበት ፖሊሲ ባለመኖሩ በንግድ ሥራ ላይ እና በኢንቨስትመንት ልማት ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል ብለዋል፡፡


117 ዓመታት እድሜ ያለው የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር እስካሁን ድረስ ተግባራዊ የሆኑ የንግድ ፖሊሲዎች የሉትም ተብላል፡፡


ለዚህም የንግድ ፖሊሲ ማሰናዳት አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ ፖሊሲው ፀድቆ ወደ ተግባር ሲገባ መስኩ የሚመራበት ወጥ የሆነ ስርዓት ይኖረዋል ብለዋል፡፡


በኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ የንግድ ሥርዓትን በአግባቡ የሚመራ ወጥ የሆነ የንግድ ፖሊሲ ስላልነበራት የንግድ ሥርዓቱ በበርካታ ችግሮች እንዲተበተብ ምክንያት ሆኗል ተብሏል፡፡

ለምሳሌም የገቢ ንግዱ ወጥ በሆነ እሳቤና አደረጃጀት እየተመራ አለመሆኑ የወጪ ንግድም በተመጣጠነ ሁኔታ በበርካታ ተቋማት የሚመራ አለመሆኑ በምሳሌት ተነስቷል፡፡


የንግድ ፖሊሲ ሲፀድቅ ሀገራዊ ተወዳዳሪነትን የሚያሳድግ፣ የወጪ ንግድን የሚያስፋፋ፣ የውጪ ምርቶችን በዓይነትና በመጠን እንዲሁም የመዳረሻ ገበያ በማስፋት በኩልም ድርሻው ከፍተኛ ይሆናል ተብሏል፡፡


ፖሊሲው የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ በግብርና ምርቶች ላይ ያለውን ጥገኝነት በማላቀቅ የወጪ ምርትን እና አገልግሎትን ተወዳዳሪነት ለማሳደግም ይረዳል ተብሏል፡፡


በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የጅምላና የችርቻሮ ንግድ ስራዎችም በአብዛኛው መደበኛ ባልሆነ መንገድ የንግድ ድርጅቶች የሚበዙበትና እሴት የማይጨምሩ ደላሎች በስፋት የሚታዩበት ስለሆነ ፖሊሲው ይህን ለማስቀረት ተወዳዳሪ እና ውጤታማ የሆነ የሎጀስቲክስ ዘርፍ ለመዘርጋት ይረዳል ተብሎለታል፡፡


የወጪ ንግድ እንቅስቃሴ የጉምሩክ አገልግሎት ላይ የሚታየውን መዘግየት በማስቀረት ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ሲብል ሰምተናል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r


Commentaires


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page