top of page

መጋቢት 25 2017 - የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የተመሰረትኩበትን አላማ በተግባር እየኖርኩት ነው አለ፡፡

  • sheger1021fm
  • 13 hours ago
  • 1 min read

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የተመሰረትኩበትን አላማ በተግባር እየኖርኩት ነው አለ፡፡


ብሔራዊ ባንክ በበኩሉ በጤናማነት የባንክ መለኪያዎች "የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንከ እጅግ ጤናማ ባንክ ነው" ብሎታል፡፡


የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የተመሰረተበትን የ20ኛ ዓመት ክብር በዓል ማጠናቀቂያ አካሄዷል፡፡


በዚህ የማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ፣ የባንኩ ደንበኞች፣ መስራቾች፣ የተለያዩ ባንኮች ፕሬዝዳንቶች ተገኝተዋል፡፡


''የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ መሰረቱን ያደረገው አርሶ አደሮችና የህብረት ስራ ማህበራትን ነው'' ያሉት የባንኩ ፕሬዘዳንት አቶ ደርቤ አስፋው 'በዚህም' ገበሬዎችንም ሆነ ህብረት ስራ ማህበራት ስራቸው እንዲያድግ ብዙ አስተዋፅኦ አበርክቷል'' ብለዋል።


የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ አሁን ላይ አጠቃላይ ህብረቱ 189.4 ቢሊዮን ብር፣ የተቀማጭ ገንዘቡ  169.4 ቢሊዮን ብር፣ ቅርንጫሮቾቹ ደግሞ  745 መድረሳቸውን ፕሬዘዳንቱ አስረድተዋል፡፡

ከባንኩ ባለአክሲዮኖች ውስጥ 55 በመቶው አርሶ አደሮችና የህብረት ስራ ማህበራት መሆናቸውን የጠቀሱት አቶ ደርቤ በመስራቾችን ህይወትና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ባንኩ አበርክቶው ጉልህ በመሆኑ ባንኩ  የተመሰረተለትን አላማ አሳክቷል ብለዋል፡፡


ባንኩ 'ምቹ' ሲል በተገበረው የዲጂል ያለ ብድር ማስያዣ መንገድ ከ20 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር መስጠቱንም ተናግሯል።


በዝግጅቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ  ገዥ አቶ ማሞ እስመለዓለም ምህረቱ "የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ብሔራዊ ባንክ ባስቀመጣቸው የባንክ ጤናማነት መለኪያዎች እጅግ ጤናማ ነው" ብለዋል።


የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ የ20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ለአንድ ወር ለሚጠጋ ጊዜ ያከበረ ሲሆነ በዚህ ወቅትም የበጎ አድራጎት ተቋማትን መደገፍ፣ ደም ልገሳ፣ የፅዳት ዘመቻ የመሳሰሉት ሲሰራ እንደቆየ ተናግሯል፡፡


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page