top of page

መጋቢት 26 2017 - በአማራ ክልል ለሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ የማሰባሰብ ስራው ነገ ይጀመራል

  • sheger1021fm
  • 13 minutes ago
  • 1 min read

#አማራ_ክልል ለሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ የማሰባሰብ ስራው ነገ ይጀመራል፡፡


በክልሉ ባለው የፀጥታ ችግር ምክንያት ከ4 ወረዳዎች ተወካዮችን ማካተት እንዳልቻለ ኮሚሽኑ ተናግሯል፡፡


የታጠቁና በትጥቅ ትግል ላይ ያሉትንም በምክክሩ ለማሳተፍ የማደርገውን ጥረት ቀጥያለሁ ብሏል፡፡


ለሀገራዊ ምክክሩ የተሳታፊ ልየታ እና የአጀንዳ ማሰባሰብ ነገ በሚጀመርበት በአማራ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት ተወካይ ለመላክ ተቸግረው ከነበሩ ስምንት ወረዳዎች አራቱ አሁንም ተወካዮቻቸውን እንዳልላኩ ሰምተናል።


የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዋናው ምክክር ክልሉን ወክለው የሚሳተፉ ተወካዮችን ለመምረጥና አጀንዳ ለማሰባሰብ በባህርዳር ከተማ ባአሰናዳውና ከነገ ጀምሮ በሚካሄደው ጉባኤ ከአብዛኛዎቹ ወረዳዎች ተወካዮች ተገኝተውልኛል ብሏል።

ነገር ግን አራት ወረዳዎች የፀጥታ ችግሩ የባሰባቸው በመሆኑ አሁንም ተወካዮቻቸውን መርጠው መላክ እንዳልቻሉ የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ ነግረውናል።


ክልሉ በግጭት ውስጥ ሁኖ የተካሄደ ያለ የምክክር ሂደት እንደመሆኑም ፈተና እንዳለበት የጠቀሱት አቶ ጥበቡ የምክክሩን አካታችነት መርህ ለመጠበቅ ግን ጥረት እየተደረገ ነው ብለውናል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..



ትዕግስት ዘሪሁን


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page