መጋቢት 26 2017 - ''አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችው የ10 በመቶ ቀረጥ እድልም ስጋትም የያዘ ነው'' የምጣኔ ሀብት ባለሞያ አቶ ክቡር ገና
- sheger1021fm
- 14 minutes ago
- 1 min read
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የጣለችው የ10 በመቶ ቀረጥ እድልም ስጋትም የያዘ ነው ተባለ፡፡
ኢትዮጵያን ጨምሮ በ100 ሀገራት ላይ የተጣለው ቀረጥ ጣሪያው 49 በመቶ ሲሆን ኢትዮጵያ የመጨረሻ መነሻው 10 በመቶ ከተጣለባቸው ሃገራት መካከል ነች፡፡
በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የምጣኔ ሀብት ባለሞያ አቶ ክቡር ገና ከሌሎች ሀገራት አንፃር በኢትዮጵያ ላይ የጣለው ቀረጥ ዝቅተኛ በመሆኑ ከሌሎቹ አንፃር በተሻለ ዋጋ ምርቷን ማቅረብ ስለምትችል ተወዳዳሪ ሊያደርጋት ይችላል ብለዋል፡፡
ይህም እንደ በጎ ጎን የሚታይ ነው ያሉት የምጣኔ ሐብት ባለሞያው፤ 10 በመቶም ቢሆን ከበፊቱ ምርቶቿ ላይ ጭማሪ ስለሚኖር የገበያ መቀዛቀዝ ሊያጋጥማት እንደሚችልም ስጋታቸውን ተናግረዋል፡፡
የአሜሪካ አዲሱ ታሪፍ ኢትዮጵያ የፖሊሲ ለውጥ አድርጋ ምርቶቿን ወደ ሌሎች ሀገራት ለመላክ ገበያ ለማፈላለግ ሊያስገድዳት የሚችል መሆኑንም አቶ ክቡር ነግረውናል፡፡
ቡና እና የጨርቃ ጨርቅ ምርቶች ኢትዮጵያ በብዛት ወደ አሜሪካ ከምትልካቸው ምርቶች መካከል ቀዳሚዎቹ ናቸው ተብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..
ንጋቱ ረጋሳ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2