መጋቢት 27 2017 - አዋሽ ባንክ ለሌሎች ባንኮች የውጭ ምንዛሪ እገዛ እያደረገ መሆኑን ተናገረ
- sheger1021fm
- 11 minutes ago
- 1 min read
አዋሽ ባንክ ለሌሎች ባንኮች የውጭ ምንዛሪ እገዛ እያደረገ መሆኑን ተናገረ።
በሦስት ወራት ውስጥ ከ498 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለደንበኞቹ ማቅረቡን አስረድቷል።
ባንኩ ከ498 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ያቀረበው እ.አ.አ ከ01/01/2025 እስከ 31/03/2025 ባሉ ሦስት ወራት ብቻ መሆኑን አስረድቷል።
ዶላሩ የቀረበውም ከ2,200 በላይ ለሆኑ ደንበኞቹ መሆኑን ጠቅሷል።
ለተለያዩ የሀገር ውስጥ ባንኮች ከ100 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ እገዛ ማድረጉን ባንኩ ተናግሯል።
አዋሽ ባንክ የደንበኞቹን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎት ለማርካት የአቅርቦት ችግር የለብኝም፣ አሁንም በእጄ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪ በሰፊው እያቀረብኩ እቀጥላለሁ ሲል ለሸገር በላከው መግለጫ አስረድቷል።
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comments