መጋቢት 27 2017 -‘’የእርስ በእርስ መጨራረስን በቃ ልንል ይገባል’’ ኮሚሽነር መላኩ ወ/ማርያም
- sheger1021fm
- 2 hours ago
- 1 min read
‘’ወንድም ወንድሙን ገድሎ ጀግንነት ስለሌለ የእርስ በእርስ መጨራረስን በቃ ልንል ይገባል’’ ሲሉ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም ተናገሩ፡፡
ኮሚሽነሩ ‘’እናቶች የሚያለቅሱበት፣ ወላጆች ልጅ አልባ የሚሆኑት ዘመን ሊያበቃ ይገባልም’’ ብለዋል፡፡
ኮሚሽነሩ ይህን የተናገሩት የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የ267 ወረዳ ተሳታፊዎች በተገኙበት በአማራ ክልል የምክክር ምዕራፍ ማስጀመርያ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም እርስ በእርስ መገዳዳል፣ መጨራረስ በቃ ልንል ይገባል ብለዋል ባደረጉት ንግግር፡፡
ምክትል ኮሚሽነር ሒሩት ገ/ስላሴ በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር ‘’የትጥቅ ትግል ጊዜያዊ ትንንሽ ድሎችን ይሰጥ ይሆናል እንጂ ሰላም’’ አይሰጥም፡፡ ሰላምን ሊሰጥ የሚችለው ቁጭ ብሎ መነጋገር ነው ብለዋል፡፡

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕ/ር መስፍን አርአያ በሚካሄዱ ግጭቶች ወጣቶች ህልማቸውን እንዳይኖሩ አድርጓል፣ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ለይቷል ብለዋል፡፡ ይህን ለመፍታት ደግሞ ምክክር ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ታጣቂዎችን ጨምሮ ሁሉንም አካላት ለማሳተፍ ኮሚሽኑ ያለሰለሰ ጥረት ሲደርግ መቆየቱን የተናገሩት ዋና ኮሚሽነሩ መስፍን አርአያ የምክክር ሂደቱ አካታች መሆን እንዳለበት ኮሚሽኑ በጽኑ ከማመን ባለፈ ህጋዊ ግዴታው እንደሆነ በቅጡ ይነዘባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ለዚህም በክልሉ ያሉ ታጣቂ ወገኖች ሁሉም እንዲሳተፉ ለማድረግ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል፡፡ አሁንም ኮሚሽኑ ሁሉም አካላት በምክክሩ እንዲሳተፉ ዳግም ጥሪ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
📌Spotify : https://shorturl.at/QG8f2
Comments