top of page

መጋቢት 29 2017 - አዋሽ ኢንሹራንስ ዓመታዊ የደንበኞች ሳምንት ማክበሬን ጀመርኩ አለ

  • sheger1021fm
  • Apr 7
  • 1 min read

አዋሽ ኢንሹራንስ ዓመታዊ የደንበኞች ሳምንት ማክበሬን ጀመርኩ አለ፡፡


መረሀ ግብሩ ከዛሬ ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚያ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ለአንድ ሳምንት የሚቆይ በሁሉም የአዋሽ ኢንሹራንስ እና አገናኝ ቢሮዎች ይከናወናል ብሏል።


ይሄው መረሀ ግብር ከዚህ በፊት ከነበሩት የደንበኞች ሳምንት የተለየ እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን የተናገረው አዋሽ ኢንሹራንስ በዚሁ ጊዜ ወደ ኩባንያው ለሚመጡ ደንበኞች ልዩ ልዩ ስጦታዎችን አዘጋጅቻለሁ ሲል አስረድቷል።


በዚህም በተለያዩ የኢንሹራንስ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በትምህርት ኢንሹራንስ፣ በሰራተኞች ኢንሹራንስ፣ በእሳት አደጋና መብረቅ ኢንሹራንስ፣ በ ‘’Mortgage Redemption’’ እና በ ‘’Individual life’’ ኢንሹራንስ ላይ እስከ 25 በመቶ የሚደርስ ቅናሽ ማድረጉን ተናግሯል።

ለተሽከርካሪያቸው ሙሉ የመድን ሽፋን ለሚገዙ ደንበኞች የሶስተኛ ወገን ሽፋን ያለ ተጨማሪ ክፍያን እንደሚሰጥ ኩባንያው አስረድቷል፡፡


200,000 ብር የነበረው የንብረት ሽፋን ወደ 300,000ብር ፣ 250,000 ብር የነበረውን የሞት እና የአካል ጉዳት ካሳ ሽፋን ወደ 300,000 ብር ከፍ እንዲል አድርጊያለሁ ብሏል።


ወደ ኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት፣ ቅርንጫፎች እና አገናኝ ቢሮዎች በመሄድ የመድህን ዋስትና አገልግሎት የሚገዙ እና ፖሊሲ የሚያድሱ ነባር ደንበኞችም ሆነ አዳዲስ ደንበኞች የአገልግሎት ተጠቃሚ ትሆናላችሁ ብሏችኋል።


"እምነትዎን ስለጣሉብን እናመሰግናለን" በሚል ሀሳብ ለሳምንት የሚቆየው ይሄው መረሀ ግብር ደንበኞችን ለማመስገንና እውቅና ለመስጠት፣ አዳዲስ ደንበኞችን ለማፍራት እና ከአገልግሎት አሰጣጡ ጋር በተገናኘ በደንበኞች አስተያየት መሰረት ክፍተቶችን ለይቶ የተሻለ አገልግሎትን ለማቅረብ ያለመ ነው ተብሎለታል።


በጠቅላላ መድህን ዘርፍ ለ30 ዓመታታት በዘርፉ የቆየው አዋሽ ኢንሹራንስ ኩባንያ ለደንበኞቼ የምሰጠውን አገልግሎት ለማዘመን የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን እየተጠቀምኩ ነው ብሏል።


በኢትዮጵያ 70 ያህል ቅርንጫፎች ያለው ኩባንያው ከ85 ሺህ በላይ የመድህን ዋስትና ተጠቃሚ ደንበኞች እንዳሉትም ተናግሯል።


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page