top of page

መጋቢት 3 2017 - 80 በመቶ የመንግስት የጤና ተቋማት መድኃኒት በብድር እንደሚገዙ ተነግሯል

ከመድሃኒት አቅርቦት ጋር ተያይዞ 80 በመቶ የሚሆኑት የጤና ተቋማት በብድር እንደሚገዙ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ተናገረ፡፡


የመድኃኒት አቅርቦት ችግር ከጊዜ ወደጊዜ እንዳይሻሻል ካደረጉት መካከል አንዱ የብድር ጉዳይ ቢሆንም የተቋማት አለመናበብ #ግጭቶችና ሌሎችም የራሳቸውን ተጽዕኖ እንዳሳደሩ ተቋሙ አስረድቷል፡፡


ይህ በጥናት መረጋገጡን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ተናግረዋል፡፡


ለማህበረሰብ #የጤና_መድህን አገልግሎት ከ 50 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ቢመዘገቡ የመድኃኒት ፍላጎትና አቅርቦት ሊመጣጠን እንዳልቻለም ተነስቷል፡፡


የጤና ተቋማቱ የወሰዱትን ብድር በወቅቱ ባለመመለሳቸው የመድኃኒት አቅርቦቱ ላይ ጫና ማሳደሩንና መድሃኒቱን መልሶ ለመግዛት እንዳልተቻለ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

80 በመቶ የመንግስት የጤና ተቋማት መድኃኒት በብድር እንደሚገዙ ተነግሯል፡፡


ይህንን ተከትሎ የጤና ሚኒስቴር ሀገር አቀፍ ጥናት ማድረጉንም ሰምተናል፡፡


ሀገር አቀፍ ጥናቱ ከመድኃኒት አቅርቦት ጋር በተያያዘ የበጀቱ ጉዳይ ምን ይመስላል የሚለው እንደሆነ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡


በዚህም በ145 ተቋማት ላይ ጥናት ተደርጓል ተብሏል፤ ጥናቱም ከአራት ሰው አንድ ሰው መድሐኒት ማግኘት እንደማይችል አሳይቷል ተብሏል፡፡


በፌደራልም ይሁን በክልል ለመድሃኒት ግዢ ዝቅተኛ በጀት እንደሚያዝም ተነግሯል፡፡


በቅርቡ የወጣው የጤና ሚኒስቴር የጤና ቁጥጥር አዋጅ የትኛውም ወጪ በጤና ተቋማት ላይ የሚደረግ በኢንሹራንስ ካልተሸፈነ በመንግስት ወይም በሌላ አካል እንዲሸፈን የሚያዝ ሲሆን ይህም የጤና ተቋማቱ የወሰዱትን ብድር መክፈል ካልቻሉ ሌላ አካል እንዲከፍልላቸው የሚያሳይ ነውም ተብሏል፡፡


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page