በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ቀውስ በተመለከተ ከፌዴራል መንግስት ጋር ለመመካከር ወደ አዲስ አበባ መምጣታቸውን የክልሉ አስተዳደር ፕሬዘዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ፡፡
ክልሉ እየታመሰ እና ጊዜያዊ አስተዳደሩም እየተፈተነ ያለው በፖሊስ አካላት ብቻ ሥርዓት መያዝ በሚችሉ ችግሮች ነው ሲሉም ከደቂቃዎች በፊት በአዲስ አበባ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል፡፡፡
በመሆኑም ክልሉ የፌዴራል መንግስቱ አካል እንደመሆኑ ክልሉ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ዳግም እንዳይገባ ሁሉንም አማራጮችና እርምጃዎች ሁሉ መውሰድ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት ትጥቅ አስፈትቶ መልሶ ማቋቋም ባለመቻሉ በትግራይ ግዙፍ የታጠቀ ሀይል መኖሩን አቶ ጌታቸው ጠቅሰዋል፡፡
ለጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር አለመግባባት ውስጥ ከገባው የሕወሃት ቡድን ጋር የጥቅምና ሌላም ትስስር ያለው የታጠቀው የተወሰነ የሰራዊቱን አካል ችግር እየፈጠረ መሆኑንም በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
የፌዴራል መንግስት አግባብነት ያላቸውን እርምጃዎች ይውሰድ ስንልም ጦር አዘምቶ ጦርነት ይቀሰቅስ እያልን አይደለም ያሉት አቶ ጌታቸው ወደ ጦርነት እያንዣበበ ያለውን ሁኔታ ለማስቀረት ሁሉንም ዓይነት እርምጃ እንዲወስድ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡
በድምፅ ያድምጡ…
ትዕግስት ዘሪሁን
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments