‘’’የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ዛሬም ድረስ መፍትሄ አልሰጠንም’’ ሲሉ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የመጡ ስራ ፈላጊ ወጣቶች ተናገሩ፡፡
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ስልጠናውን ሲሰጠን እና ሲያስተምረን ትሄዳላችሁ ብሎ ቃል የገባልን ወደ አውሮፓ ሀገራት እንጂ ወደ አረብ ሀገር እንዳልሆነ ነግሯቸው እንደነበር ወጣቶቹ አስረድቷል፡፡
ትምህርቱን ካጠናቀቅ በኋላ ስራውም የለም የምትሄዱትም አረብ ሀገር ነው ሲል ነግሩናል ይላሉ፡፡
ወጣቶቹ እንደሚሉት ከሆነ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሁለት መቶ በላይ የሰው ኃይል እንደሚያስፈልገው እና እጥረት እንዳለበት ቢናገርም ለእኛ ስድስት ሺህ ለምንሆን ወጣቶች የስራ ድል ሊፈጥርልን አልቻለም ብሏል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ቃል በገባልን መሠረት ወደተባለው #አውሮፓ ሀገራት ባይልከንም እኛ በራሳችንን ስራ ስላገኘን ወደ ኤምባሲዎች የምንገባበት መንገድ ያመቻችልን ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አልቆላችሁ ትሄዳላችሁ ተብለን ከዓመት በላይ ያለ ስራ እንደተቀመጡ ተናግረዋል፡፡
አረብ ሀገር ሳይሆን ወደ አውሮፓ ነው የምትሄዱ ተብለናል ስንል የተቋሙ ሰራተኞች አውሮፓ ሀገር ቢኖር እኛም እንሄዳለን እያሉ ያሾፍብናል ብለዋል ወጣቶቹ፡፡
መንግስትን ተስፋ አድርገን የስራ እድል ተፈጠረልን ብለን ብንመጣም እንኳን ስራ ልናገኝ የነበረንን ስራ እንድናጣ ሆነናል ብለዋል፡፡
የስራና ክህሎት ሚኒስቴርን ለተነሳው ቅሬታ መልስ እንዲሰጥ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም መልስ መስጠት አልቻለም፡፡
ከዚህ ቀደም በሰራነው ተመሳሳይ ዘገባ የኤጀንሲዎች አሰሪዎች ፌዴሬሽን ክፍተቱ የኛ ሳይሆን የስራና ክህሎት ነው ማለት ይታወሳል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ……
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comentarios