top of page

መጋቢት 5 2017 - የፓለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና በክልሉ ያለው ግጭት እንዲቆም ኮሚሽኑ ጠየቀ፡፡

የፓለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና በክልሉ ያለው ግጭት እንዲቆም ኮሚሽኑ ጠየቀ፡፡


የተኩስ አቁም በማወጅም መንግስት ቀዳሚውን እርምጃ በመውሰድ ሰላም ንግገር እንዲገባም ተጠይቋል፡፡


በዋና ኮሚሽነሩ ፕሮፌሰር መስፍን ዓርዓያ የተመራ ልዑክ ትላንት ወደ #አማራ_ክልል ባህርዳር ከተማ አቅንቶ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ማድረጉን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል ተብሏል፡፡


የኮሚሽኑ ልዑክ ወደ አማራ ክልል ያቀናው የአማራ ክልል የአጃንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ በሚካሄድበት አስቻይ ሁኔታ ላይ ከክልሉ መንግስት ጋር ለመነጋገር ነው።

ኮሚሽኑ ምክክሩን አካታች በሆነ ሁኔታ ማከናወን እንዲችል በማንኛውም አካባቢ በ #ፖለቲካ ጉዳዮች ምክንያት የታሰሩ እስረኞች እንዲፈቱ የክልሉ መንግስት በራሱ በኩል እርምጃ እንዲወስድ እንዲሁም በሌሎች ላይም ግፊት እንዲያደርግ ልዑኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር በተገኙበት ጥያቄ አቅርቧል ተብሏል፡፡


በክልሉ ያለው ግጭት ቆሞ አስቻይ የምክክር ሁኔታ እንዲኖር ራሱ የክልሉ መንግስት ተኩስ አቁሜአለሁ ብሎ በማወጅ የመጀመሪያውን እርምጃ እንዲወስድም ነው የኮሚሽኑ ልዑክ ጠይቋል፡፡


ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ በበኩላቸው የክልሉ መንግስት ለኮሚሽኑ ስራ መሳካት እስካሁን ሲያደርግ እንደነበረው ሁሉ በክልሉ የሚያካሂደው የምክክር መድረክ እንዲሳካም ድጋፉን እንደሚቀጥል ተናግረዋል ተብሏል፡፡


ምክክሩ አሳታፊና አካታች በሆነ አስቻይ ሁኔታ እንዲካሄድም ኮሚሽኑ ያቀረባቸው ጥያቄዎች በክልሉ መንግስት በኩል ተገቢው ትኩረት ይሰጣቸዋል ብለዋል፡፡

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page