ህብረት ባንክ የ50 ሚሊዮን ድርሻ በመግዛት 4ተኛው የግል ባንክ ሆኗል፡፡
ከዚህ ቀደም ዘመን ባንክ፣ ሲንቄ ባንክ እና ግሎባል ባንክ የ 50 ሚሊዮን ድርሻ ሲገዙ አዋሽ ባንክ የ 70 ሚሊዮን ድርሻ ከሰነዶች ሙዓለ ነዋይ መግዛቱ ይታወቃል፡፡
የካፒታል ገበያ በኢትዮጵያ ስራ መጀመሩን ተከትሎ የፋይናንስ ተቋሞች ከሰነድ ሙዓለ ነዋይ ገበያ ድርሻ መግዛታቸው፤ በኢትዮጵያ የተጀመረውን የካፒታል ገበያ ወደፊት እያበረታታው መሆኑ ከዚ ቀደም ተነግሯል፡፡
የኢትዮጵያ የሰነድ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ጥላሁን እስማኤል፤ ህብረት ባንክ ይህንን ድርሻ ከገበያው መግዛቱ የካፒታል ገበያው በብርቱ እንዲገጓዝ ያግዛል ብለዋል፡፡
የህብረት ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ከበደ ይህ መንገድ ለፋይናንስ ሴክተሩ ብቻ ሳይሆን ለአጠቃላይ ኢኮኖሚው የሚጠቅም መፍትሄ አለው ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ፣ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት እንዲሁም ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት መስራች አባል መሆን የሚያስችላቸውን የ25 በመቶ ድርሻ ከኢትዮጵያ የሰነድ መዋለ ነዋይ ገበያ ገዝተዋል፡፡
ወሬውን የኢትዮጵያ የሰነዶች ሙዓለ ንዋይ ገበያ ለሸገር ነግሯል፡፡
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments