38 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች በሰሜናዊ ጅቡቲ በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ ሕይወታቸውን አጥተዋል ተባለ።
በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ የመን በመጓዝ ላይ በነበረች ጀልባ ላይ በደረሰ የመስጠም አደጋ 38 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን አጥተዋል ያለው በጂቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ነው።
አደጋው የደረሰው ትላንት መጋቢት 30/2016 ዓ.ም በጅቡቲ ሰሜን ምስራቅ ጎዶሪያ በሚባል የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ነው ተብሏል፡፡
60 ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞችን አሳፍራ ወደ የመን ትጓዝ የነበረች ጀልባ ላይ በደረሰው የመገልበጥ አደጋ የ 38 ፍልሰተኞች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በጅቡቲ የኢፌዴሪ ሚሲዮንም አደጋው ከደረሰ በኋላ ወደ ስፍራው በመጓዝ የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እገኛለሁ ብሏል።
ባለፉት አምስት ዓመታት በጀልባ መስመጥ አደጋ ብቻ የ189 ኢትዮጵያዊያን ሕይወት ማለፉን ኤምባሲው አስታውሷል።
በየጊዜው የሚደርሰው አደጋ እንዳለ ቢሆንም የፍልሰተኞቹ ቁጥር ግን አሁንም እየጨመረ ነው ተብሏል።
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: @ShegerFMRadio102_1
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments