ሚያዝያ 11 2017 - በዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ የኢ-ኮሜርስ አገልግሎት መጀመሩን ተናገሩ
- sheger1021fm
- 6 minutes ago
- 1 min read
በዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ የኢ-ኮሜርስ አገልግሎት መጀመሩን ተናገሩ።
በፋይናንስ ኢንዱስትሪው አዳዲስ የዲጂታል ግኝቶችን እያስተዋወቀ እንደሆነ የተናገረው ዳሸን ባንክ፣ በዳሸን ሱፐር አፕ የኢ-ኮሜርስ አገልግሎት መጀመሩን ተናግሯል።
ደንበኞች በዳሸን ሱፐር አፕ ለበዓል የሚያስፈልጋቸውን የበሬ ቅርጫ፣ የበግ እና የዶሮ ስጋ አንቁላልን ጨምሮ አልባሳት፣ ለስጦታ የሚሆኑ ሰዓትና ቀለበቶች፣ ዘመናዊ የቆዳ ቦርሳዎች ዘመናዊ ጫማዎች፣ የባልትና ወጤቶች እና ሌሎች በርካታ ምርቶችን በቀላሉ መገበያየት ይችላሉ ሲል ለሸገር በላከው መግለጫ አስረድቷል፡፡
ዳሸን ባንክ ይፋ ያደረገው የኢ-ኮሜርስ አገልግሎት ደንበኞች በዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ የፈለጉትን እቃ በቀላሉ ሲያዙ፣ ከየትኛውም የአዲስ አበባ አካባቢ ባሉበት ሆነው የታዘዘው ዕቃ በፍጥነት የሚደርሳቸው ይሆናል ተብሏል፡፡
ዳሸን ባንክ ሱፐር አፕ የኢ-ኮሜርስ አገልግሎት ሌሎች አዳዲስ አገልግሎቶችን ይዞ እየመጣ እንደሚገኝ ባንኩ አስረድቷል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments