ሚያዝያ 14 2017 - ለጤና ጠንቅ የሆኑ የምግብ ምርቶችን ይዘው የተገኙ 14 ተቋማት መታሸጋቸው ተሰማ
- sheger1021fm
- 7 minutes ago
- 1 min read
የፋሲካ በዓልን ምክንያት አድርገው ለጤና ጠንቅ የሆኑ የምግብ ምርቶችን ይዘው የተገኙ 14 ተቋማት መታሸጋቸው ተሰማ፡፡
ለገበያ ቀርበው ነበር ከተባሉት ምርቶች መካከል የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ይገኙበታል፡፡
የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ከወንኩት ባለው የቁጥጥር ስራ ለበዓሉ ሊኖር የሚችለውን የማህበረሰቡን የመሸመት ፍላጎት ባልተገባ መንገድ ሲጠቀሙ ያገኋቸውን 14 ተቋማት አሽጊያቸዋለሁ ብሎናል፡፡
ተቋማቱም የምግብ ዘይት ማምረቻዎች፣ የ #ባልትና ውጤት መሸጫዎችና ወፍጮ ቤቶች መሆናቸውን የነገሩን በአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወ/ሮ ወርቅነሽ ብርቄ ናቸው፡፡
በክትትሉ የተገኙት የምግብ ምርቶች ምን አይነት የጤና እክል ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ናሙና ተወስዶ በላብራቶሪ ምርመራ እየተደረገበት ነው፤የላብራቶሪ ውጤቱ ታይቶ ተጨማሪ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡
በዓሉን ተከትሎ ሊኖር የሚችልን የምርትና ሽያጭ ወቅት ችግር ለመቆጣጠር በተደረገው ክትትል የተፈተሹት 2500 ተቋማት ናቸው ያሉን ሃላፊዋ ከእነዚህ ውስጥ 14 ታሽገዋል፤ 82ቱ በፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ታልፈዋል፤ ቀሪዎቹ እንከል እንዳልተገኘባቸው ጠቅሰዋል፡፡
የታሸጉት የምግብ ዘይት ፋብሪካዎች፣ ባልትና መሸጫዎችና ወፍጮ ቤቶች ወደ ቀደመ ስራቸው ለመመለስ የተገኘባቸውን ችግር ማስተካከላቸውን ለባለስልጣኑ ያሳውቃሉ፤ተቆጣጣሪው ባለስልጣንም ችግሩ መስተካከሉን ሲያረጋግጥ እንዲከፍቱ ይፈቅድላቸዋል ብለውናል ወ/ሮ ወርቅነሽ፡፡
በተጨማሪም በቁጥጥር ስራው ከ2መቶ ሺህ ብር በላይ ዋጋቸው የተገመተ ምግብና መጠጦችን ባለስልጣኑ የማህበረሰቡ የጤና ጠንቅ ናቸው ሲል ከገበያ ሰብስቦ ማስወገዱንም ከሃላፊዋ ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ምንታምር ፀጋው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
תגובות