ሚያዝያ 14 2017 - በጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት ላይ፤ ወጥ የሆነ ዋጋ እንዲኖረው ሊደረግ መሆኑ ተሰማ
- sheger1021fm
- 6 minutes ago
- 1 min read
በጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይት ላይ፤ ወጥ የሆነ ዋጋ እንዲኖረው ሊደረግ መሆኑ ተሰማ።
የጥሬ ቆዳና ሌጦ ግብይትን በተመለከተ የዋጋ ወጥነት ባለመኖሩ በተለይ በበዓላት ወቅት በየመንገዱ እንዲወድቅ ምክንያት መሆኑ ተነግሯል።
ይህንን እና መሰል ችግሮችን ይቀርፋል፣ የተባለለት ይህ አሰራር በቅርቡም ወደ ስራ እንደሚገባም የነገረን የቆዳና ቆዳ ውጤቶች ኢንደስትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል ነው።
በአምራች ኢንደስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ቆዳና #የቆዳ_ውጤቶች ኢንደስትሪ ግብአት ዴስክ ሀላፊ አቶ ታረቀኝ ዲዳ ይሄ አሰራር ተግባራዊ ሲደረግ ነጋዴዎች አላግባብ የሚጥሉትን ዋጋ እንዲቆጣጠር ያስችላል ብለዋል።

ከዚህ ቀደም በቆዳው ዘርፍ የተሰማሩ አምራቾች ከዘርፉ የወጡ እንደነበሩ ያስታወሱት አቶ ታረቀኝ በዘርፉ የወጡበት ምክንያት የገበያ ትስስር፣ የኬሚካል አቅርቦት እና የጨው አቅርቦት አለመኖር እንዲሁም መሰል ችግሮች ስለነበሩ ነው ሲሉ አስረድተዋል።
አሁን ላይ ግን በተወሰነ መልኩ የተፈቱ ችግሮች ቢኖሩም የኬሚካል አቅርቦት ግን አሁንም ዘርፉን እየፈተነው መሆኑን ነግረውናል።
ከዚህ ቀደም በየመንገዱ ይጣል የነበረው ቆዳ አሁን እምብዛም አይታይም ያሉን አቶ ታረቀኝ በማህበረሰቡ በኩል ግን አሁንም ቆዳ ዋጋ የሌለው አይነት አመለካከት እንዳለም ተናግረዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments