top of page

ሚያዝያ 15 2017 - ‘’በአዲስ የተዋቀረው ካቢኔ በክልሉ ባለፉት 2 ዓመታት ታይቶ የነበረውን የዴሞከራሲ ልምምድ ወደ ቀድሞው የሚመልስ ነው’’ ተፎካካሪ ፓርቲዎች

  • sheger1021fm
  • 28 minutes ago
  • 1 min read

በአዲስ የተዋቀረው ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ በክልሉ ባለፉት ሁለት ዓመታት ታይቶ የነበረውን የዴሞከራሲ ልምምድ ወደ ቀድሞው ቦታው የሚመልስ ነው ሲሉ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሶስት ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተናገሩ፡፡


የአዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ አካታች ያልሆነ፤ ለክልሉም ሰላም የማያመጣ ነው ሲሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተችተዋል፡፡


በአዲሱ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዘዳንት በሌተና ጀነራል ታደሰ ወረደ ባለፈው የተዋቀረው ካቢኔ አካታች ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲኖር የሚያዘውን የሰላም ስምምነት የሚጥስ ነው ሲሉ ፓርቲዎቹ ተናግረዋል፡፡


በአዲሱ ካቢኔ ላይ ትችት ያቀረቡት ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ ባይቶና እና አረና ፓርቲዎች ናቸው፡፡


ፓርቲዎቹ በአዲሱ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዘዳንት በጀነራል ታደሰ ወረደ የተዋቀረው ካቢኔ፤ ደብረፅዮን ገ/ሚካዔል(ዶ/ር) የሚመራው የህወሓት ቡድንን ወደ ቦታው እንዲመለስ ያደረገ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡


አዲሱን ካቢኔ የቀድሞው የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዘዳንት የነበሩት የአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን መቃወሙ ተሰምቷል፡፡


ይሁንና በአቶ ጌታቸው ቡድንም ይሁን ፓርቲዎች በቀረቡት ትችት ላይ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….




ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page