top of page

ሚያዝያ 15 2017 - ደንብ ተላላፊዎች ላይ የተጣለው ቅጣት ከፍ ማለቱ በከተማዋ በሚታየው ሥርዓት ይዞ አለማሽከርከር ላይ ምን ለውጥ አመጣ ?

  • sheger1021fm
  • 30 minutes ago
  • 1 min read

በቅርብ ጊዜ ተግባራዊ በተደረገው የትራፊክ ደንብ ጥሰት ቅጣት የተነሳ አሽከርካሪዎች ሲማረሩ ይሰማል፡፡


የቅጣት መጠኑ ከፍ ማለቱ አጥፊ አሽከርካሪዎችን እንዲሰማቸው እያደረገ ነው መባሉንም ሰምተናል፡፡


ለመሆኑ የትራፊክ ደንብ ተላላፊዎች ላይ የተጣለው ቅጣት ከፍ ማለቱ በከተማዋ በሚታየው ሥርዓት ይዞ አለማሽከርከር ላይ ምን ለውጥ አመጣ ?


የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ኤሊያስ ዘርጋ ነባሩ የትራፊክ መቆጣጠሪያ ደንብ የገንዘብ ቅጣቱ አነስተኛ በመሆኑ ደንብ የሚተላለፉ አሽከርካሪዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ፣ በትራፊክ አደጋም የሚጎዳው የህብረተሰብ ቁጥር እያሻቀበ በመሆኑ በአዲሱ ደንብ የቅጣት መጠኑን ከፍ ማድረግ አስፈልጓል ብለዋል፡፡


ነዳጅ በመወደዱ ቅጣቱ ይቀንስልን የሚል አስተያየትና መከራከሪያ ነጥብ ተቀባይነት አይኖረውም ሲሉም ይናገራሉ፡፡


በአዲሱ ደንብ የገንዘብ ቅጣቱ ከፍ እንዲል መደረጉም የትራፊክ ደንብ ጥሰቶችን እንዲቀንሱ አስችሏል ሲሉም ኢንጂነር ኤልያስ ተናግረዋል፡፡


አሽከርካሪዎች በየጊዜው ከሚያነሷቸው ቅሬታዎች መካከል ደግሞ ባላጠፋነው ደንብ እየተቀጣን ነው፤ ለተቆጣጣሪ መስሪያ ቤትም አቤቱታ ብናቀርብም ፍትህ እያገኘን አይደለም የሚል ነው፡፡


ይህን በተመለከተም ኢንጂነር ኤልያስ አብዛኛው የሚመጣው ቅሬታ ተገቢነት የሌለው ነው ብለዋል፡፡


የትራፊክ ምልክቶች በሌሉበት የሚቀጣ ተቆጣጣሪ ፖሊስ ካለ እርምጃ እንወስዳለን፣ የትራፊክ ምልክት በግልፅ በማይታይበት እና በሌለበት ተቀጣን የሚሉ ካሉም ያሳውቁን ሲሉ ኢንጂነር ኤልያስ ተናግረዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….




ፍቅሩ አምባቸው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Commentaires


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page