በኢትዮጵያ ህግ መሰረት እድሜያቸው አስራ ስምንት ዓመት ያልሞላቸው ህፃናት አካላዊም ሆነ አዕምሯዊ ጉዳት የሚያስከትልባቸው ስራ እንዳይሰሩ ህጉ ይደነግጋል፡፡
ይሁንና የገጠሪቷን ኢትዮጵያ ጨምሮ ብዙ ደሀ ቤተሰብ እና ህፃናት በሞሉባት ሀገራችን ህፃናትን ይህን ስሩ ይህን አትስሩ ብሎ መገደብ ይቻላል ወይ? ሲሉ የሚጠይቁ በርካቶች ቢኖሩም ጉዳዩ አከራካ ሆኖ ቀጥሏል፡፡
የሚላስ የሚቀመስ የሌለው ቤተሰብ ልጁ አስራ ስምንት ዓመት እስኪሞላው ከብት መጠበቅም ሆነ እንጨት መልቀምን እንደምን ሊከላከል ይቻለዋል?
በህፃናት የጉልበት ስራ ዙሪያ የሚመለከታቸውን አነጋግረናል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: @ShegerFMRadio102_1
Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio
Website: https://www.shegerfm.com/
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentarios