በኢትዮጵያ የሴት ልጅ የተፈጥሮ ዑደት የሆነው የወር አበባ ከነውር መቆጠሩ አሁንም አልቀረም።
በተለይ ትምህርት ባልተስፋፋበት፣ ሴቶች ዕድሜያቸው ለአካለ መጠን ሳይደርሱ ለጋብቻ በሚታጩበት የገጠሩ ማኅበረሰብ ውስጥ የወር አበባ ጉዳይ ሸክሙ ይከብዳል።
ልጃገረዶች በትምህርት ቤት ሳሉ ድንገት የወር አበባቸው መጥቶ ደም ቢፈሳቸው፤ "አይዞሽ" ከመባል ይልቅ መሳቂያ፣ መሳለቂያና ጣት መጠቋቆሚያ ይሆናሉ።
ይህን በመፍራት ብዙ ልጃገረዶች ገና የወር አበባቸው መምጫ መቃረቡን ሲያስቡ ይሸበራሉ፣ ከትምህርት ቤትም ይቀራሉ፣ ትምህርታቸው ለብዙ ቀናት ይስተጓጎላል፤ በዚያው መጠን ከትምህርቱ ወደኋላ ይቀራሉ።
መንግሥትም ሞዴስ በሀገር ውስጥ የሚያመርቱ ፋብሪካዎች ከውጭ ለሚያስገቡት ጥሬ እቃ ከታክስ ነፃ እንዲሆኑ ንፅህና መጠበቂያዎቹ ከውጭ ሲገቡ ደግሞ ታክሱ 10 ከመቶ እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል፡፡
ዋጋው በመወደዱ ምክንያት ምርቶቹን የሚጠቀሙ የሴቶች ቁጥር 25 በመቶ ብቻ መሆናቸው ጥናት አሳይቷል፡፡
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
コメント