top of page

ምጣኔ ሐብት - በፋይናንስ ዘርፉ ስላለ መረጃ አያያዝ

የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር ምን ያህ ነው?


አራሹ ገበሬ ስንት ነው፤ እርብቶ አደሩስ?


በማኑፋክቸርንግ፣ በቱሪዝም የሚተዳደረው፣ እንጀራ የሚቆርሰው ስንቱ ነው?


ስንቱ ሰው ስራ አለው፤ ስንቱስ የለውም?


ለእነዚህ እና ተመሳሳይ ጥያቄዎች ቁርጥ ያለው መረጃ ማግኘት አይቻለም፡፡


በየመድረኩ የሚነገረው፣ የሚፃፈው እዚህ አካባቢ፣ እዚህ ግድም፣ ይሄን ያህል የሚጠጋ፣ ከዚህ የሚበልጥ የሚል ነው፡፡

ቁርጥ፣ መረጃ፣ ዳታ ግን ለምንም ስራ መነሻውን የሚያስተካክል፣ መድረሻውን የሚበይን ነው፡፡


ዳታው፣ መረጃው፣ ቁጥሩ የፋይናንስ ዘርፉን፣ ገበያው፣ ባንኩን፣ ኢንሹራንሱን የሚመለከት ሲሆን ወሳኝነቱን ይበልጥ ያበረታዋል፡፡


በዚህ የምጣኔ ሐብት ዝግጅት በፋይናንስ ዘርፉ ስላለ መረጃ አያያዝ እና ተያያዥ ጉዳዮች ተነስቷል፡፡


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


bottom of page