top of page

ሰኔ 15፣ 2016 - የቤት ኪራይ ዋጋ እየጨመሩ ያሉ አከራዮች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ተናገረ

በነዋሪው ላይ የቤት ኪራይ ዋጋ እየጨመሩ ያሉ አከራዮች ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ተናገረ።


ቢሮው ይህንን ያለው በመካሄድ ላይ ያለውን የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።


ባሳለፍነው ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም በተጀመረው የአከራይ ተከራይ የውል ምዝገባ በሁሉም የአዲስ አበባ ወረዳዎች በየቀኑ እስከ 10 ሺህ እየተመዘገቡ መሆኑን የቢሮው ሃላፊ ቅድስት ተናግረዋል።


አጠቃላይ ቁጥሩን ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ እናደርጋለንም ብለዋል።


የቢሮ ሃላፊዋ እንዳሉት ምዝገባ መጀመሩን ተከትሎ አንዳንድ አከራዮች በተከራዮቻቸው ላይ ዋጋ እየጨመሩ፤ ከቤት ለማስወጣትም እየሞከሩ እንደሆነ ጥቆማ ደርሶናል ብለዋል።


የአከራይ ተከራይ አዋጅ ከወጣበት ካለፈው መጋቢት 24 2016 ዓ.ም ጀምሮ ምንም አይነት የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመር የተከለከለ ነው ብለዋል።


የኪራይ ዋጋ ጨምሮ የተገኘ አከራይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል ተብሏል።


የሚወሰዱ እርምጃዎች፦


የቤት ኪራይ ጨምሮ የሚገኝ  አከራይ የተጨመረው ገንዘብ ተቀንሶ ወደ ነበረበት ይመለሳል።


እስከ ሰኔ 30 ሳይመዘገቡ ቀርተው 3 ወራት የቆዩ እንደሆነ አከራይም ተከራይም  የ2 ወር የቤት ኪራይ ይቀጣሉ።


ህጋዊ ያልሆነ ቤት ምዝገባ ውስጥ አይገባም፤


በኪራይ ውሉ ላይ ከተቀመጠው የኪራይ ዋጋ በላይ ማስከፈል የተከለከለ ነው ተብሏል።



ምንታምር ፀጋው

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page