ይህ የተባለው በፌድሬሽን ምክር ቤት የማንነት የአስተዳደር ወሰን እና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ለፌድሬሽን ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡
ከማንነት ይታወቅልኝ እና መካለል ጋር በተያያዘ የወልቃይት የራያ እና የጠለምት ማህበረሰቦች ያነሷቸውን ጥያቄዎች በተመለከተ ለውሳኔ ሂደት የሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ቢሆኑም በቦታው ተገኝተው ተጨማሪ መረጃዎችን ለመሰብሰብ በአካባቢው በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት እንዳልተቻለ ቋሚ ኮሚቴው በሪፖርቱ ተናግሯል፡፡
በዚህም በአካባቢው የሰላም ሁኔታ ሲሻሻል ጉዳዩ በቀጣይ ትኩረት ተሠጥቶት የሚሰራው ይሆኗል ሲል የፌድሬሽን ምክር ቤት የማንነት የአስተዳደር ወሰን እና የሰላም ግንባታ ቋሚ ኮሚቴ ሲናገር ሰምተናል፡
ያሬድ እንዳሻው
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Comments