ደንበኞች አገልግሎት ለማግኘት ወደ ባንክ ቅርንጫፎች መሄድን የሚያስቀረው ቨርችዋል ባንኪንግን የሚጠቀመው ተገልጋይ ቁጥር እየጨመረ ነው ተባለ፡፡
የባንኮችን ቅርንጫፍ ከመጨመር ይልቅ ቨርችዋል ባንኪንግ አገልግሎት የሚሰጡትን ማስፋት የተሸለ እንደሆነ አቢሲኒያ ባንክ ይናገራል፡፡
ባንኮች የሚከፍቱትን ቅርንጫፎች አብዝቶ 24 ሰዓት ማሰራቱ በተለያዩ ምክንያቶች ዘርፉን ውጤታማ አያደርገውም ያሉት በአቢሲኒያ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ኦፕሬሽን ክፍል ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ረታ የቨርችዋል ባንኪንግ ቴክኖሎጂው ግን አገልግሎቱን የተሸለ ያደርግልናል ብለዋል፡፡
ቴክኖሎጂው ለኢትዮጵያውያን ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ደግሞ የተጠቃሚውም ቁጥር እንዲጨምር አድርጎታል የሚሉት አቶ ዳንኤል በዚህም አቢሲኒያ ባንክ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች 35 ማእከላት ለደንበኞች አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሆኑ ተናረዋል፡፡
Comments