top of page

ሰኔ 3፣ 2016 - የሽግግር ፍትህ ፍኖተ ካርታ ተጠናቆ ለውይይት መዘጋጀቱን የፍትህ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

  • sheger1021fm
  • Jun 10, 2024
  • 1 min read

ፍኖተ ካርታው በፖሊሲ የትግበራ ምዕራፍ የሚከናወኑ ተግባራትን በዝርዝር የያዘ ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ለህዝብ ውይይት ዝግጁ መደረጉን የፍትህ ሚኒስቴር በማህበራዊ የትስስር ገፁ ላይ አስፍሯል፡፡


በተዘጋጀው ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በአባልነት የሚሳተፉበት ጊዜያዊና ዘላቂ ተቋማዊ አመራር ስርዓት ስለሚቋቋሙበት ሁኔታ፣ ይዟል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ስለሽግግር ፍትህ ስልቶች አተገባበር ቅድመ ተከተል ለሽግግር ፍትህን የሚፈፅሙ ተቋማትን ለማቋቋም ከተቋመም በኋላ ስራቸውን የሚሰሩበት ሁኔታ የሚደነግጉ የህግ ማዕቀፎች ስለሚዘጋጅበት ሁኔታም ተካቶበታል ተብሏል፡፡


በፍኖተ ካርታው በሽግግር ፍትህ ትግበራ ምዕራፍ የክልሎችን የባህላዊ ፍትህ ሥርዓቶችን የተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ሚና ተሳትፎና እንዲሁም የፆታ ጥቃት ሰለባዎችን በተመለከተ የሚተገበሩ ተጨማሪ እርምጃዎች በፍኖተ ካርታው ተካቷል ተብሏል፡፡


ከዚህ ባለፈም ስለሽግግር ፍትህ ትግበራ ህዝቡ ያለውን እውቀት ለማሳደግ ስለሚሰሩ ዝርዝር ተግባራት በፍኖተካርታው መካተታቸውን ከፍትህ ሚንስቴር ሰምተናል፡፡

Comentários


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page