top of page

ግንቦት 23፣2016 - ሴቶች በሰብአዊ መብት ጥሰት እና መሰል ፈተናዎች እየተቸገሩ መቀጠላቸው ይነገራል

ሴቶች በጤና፣ በአመራርነትና ውሳኔ ሰጭነት፣ በኢኮኖሚው እና በሌላውም መስክ ያላቸው ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ቢሆንም በሰብአዊ መብት ጥሰት እና መሰል ፈተናዎች እየተቸገሩ መቀጠላቸው ይነገራል፡፡


ይህ የተባለው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር 6ኛውን ሀገር አቀፍ የቤጂንግ ትግበራ ሪፖርት ይፋ ባደረገበት ወቅት ነው፡፡


የቤጂንግ ትግበራ ሪፖርት ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ የተነገረ ሲሆን ዘንድሮም የተመሰረተበት 30ኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ 6ኛው ሀገር አቀፍ ሪፖርት ውጤት ይፋ ተደርጓል፡፡


ስምምነቱም በ12 ዘርፎች ላይ ሴቶች ያላቸው ተሳትፎ እስከምን ድረስ ነው፣ የሚያጋጥሟቸው ችግሮች እና ለችግሮቹ የሚሰጠው መፍትሔስ ምንድን ነው የሚሉትን እና ሌሎችንም ጉዳዮች የተመለከተ የሚዳስስ ነው ተብሏል፡፡


ይህንን ለሸገር የተናገሩት በሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአካቶ ትግበራ ክትትል ድጋፍ ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ከተማ ለገሰ ካለፉት አመታት ጋር ሲነፃፀር የተሸለ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል፡፡


በሌላ በኩል ተቋማት ለስርአተ ፆታ የሚመድቡት በጀት እጥረት መኖር አንዱ ችግር እንደሆነ ግኝቱ ያሳያል የሚሉት ስራ አስፈፃሚው ጥናቱ ሲከወንም በአንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያለው የሰላም እጦትም ሌላኛው ችግር መሆኑን ተናግረዋል፡፡


ይህም ሆኖ ግን በአጠቃላይ በሁሉም ዘርፍ የተገኘው ለውጥ ከቀደሙት አመታት ጋር ሲነፃፀር ጥሩ የሚባል እንደሆነ በሪፖርቱ ያሳያል መባሉን ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ…. https://tinyurl.com/2bt97sew


ፋሲካ ሙሉወርቅ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw


Youtube: http://tiny.cc/ShegerFM1021Radio


Website: https://www.shegerfm.com/


Comentários


bottom of page