በአዲስ አበባ አንድ ኩንታል ጤፍ 13፣ 14፣15 ሺህ ብር እየተሸጠ ነው፡፡
አንድ ኪሎ ቀይ ሽንኩርት እስከ 130 ብር ሲሸጥ ታይቷል፡፡
በዚህም የተነሳ ነዋሪው ኑሮን የሚሸከምበት ትከሻው ጎብጦ ኧረ ምንድነው ነገሩ ፣ የመፍትሄ ያለህ እያለ ነው፡፡
በሀገር ቤት በጎጃም ፣ በአርሲ የምትመረተው ጤፍ ዋጋዋ እንዲህ አልቀመስ ያለው ለምንድነው?
አልፎ አልፎ ካልሆነ በስተቀር እዚሁ ሀገር የሚበቅለውን ሽንኩርት ልጣ ወጥ የምትሰራው አዲስ አበባ ሽንኩርት እንዲህ ለምን ተወደደባት?
Comments