top of page

ሐምሌ 9፣ 2016 - በምስራቅ ሀረርጌ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ‘’ሳይበሉ የሚውሉበት ቀን ትንሽ አይደለም’’ ጥናት

በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትና ማጣት ተደጋግሞ የሚነሳ ችግር ነው፡፡


#በምስራቅ_ሀረርጌ ባሉ ወረዳዎች በሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ የተጠና ጥናትም የሚያሳየው ይሄንኑ ነው፡፡


ጥናቱ በተከናወነባቸው ዘጠኝ ወረዳዎች ያሉ ነዋሪዎች የምግብ ዋስትናቸው በጣም ዝቅተኛ መሆኑ የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳይ ሲነገር ሰምተናል፡፡


‘’የምግብ ዋስትና ማጣት እንደ ሀገር ያለብን ችግር ነው’’ የሚሉት ጥናት አቅራቢዋ ሀና እንዳሻው ‘’በምስራቅ ሀረርጌ የሚታየው ደግሞ ከፍተኛ ነው’’ ብለዋል፡፡


‘’አንድ ሰው የምግብ ዋስትና አለው ወይም የለውም ሊባል የሚችለው በአራት መመዘኛዎች ነው’’ የሚሉት ጥናት አቅራቢዋ ‘’ከነዚህም መካከል በቀን ውስጥ በልቶ ይውላል ወይ የሚለው ቀዳሚው ነው’’ ብለዋል፡፡


በዚህ መሰረትም በምስራቅ ሀረርጌ የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ‘’ሳይበሉ የሚውሉበት ቀን ትንሽ አይደለም’’ ብለዋል፡፡


‘’የብድር አቅርቦት መኖር እና ከግብርና በተጨማሪ ሌሎች ስራዎችን መከወናቸው የአካባቢው ማህበረሰብ አሁን ላለበት የምግብ ዋስትና ማጣት እንዲጋለጥ ከሚያደርጉ ምክንያቶች ዋናዎቹ ናቸው’’ ብለዋል ሀና እንዳሻው፡፡


በተለይ ብድር ከወሰዱ በኋላ ምርታማነታቸው የተለየ ውጤት አለማምጣቱ እና የወለድ መጠኑ ከፍ ማለት ለችግሮቻቸው መነሻ እንደሚሆኑ በጥናቱ የተገኘው ውጤት እንደሚያሳይ ተናግረዋል፡፡


በምስራቅ ሀረርጌ ዘጠኝ ወረዳዎች 880 በሚሆኑ አባውራዎች ጥናቱ የተከወነ ሲሆን በጣም ዝቅተኛ የሆነ #የምግብ_ዋስትና እንዳላቸው ተነግሯል፡፡




ፋሲካ ሙሉወርቅ

Comments


bottom of page