top of page

በአትላንቲክ ውቅያኖስ የገባችበት የጠፋውን ቱሪስቶች መጓጓዥ ጠላቂ ጀልባ ለማግኘት ሰፊ ፍለጋ እየተካሄደ መሆኑ ተሰማ

  • sheger1021fm
  • Jun 20, 2023
  • 1 min read

ሰኔ 13፣2015


በአትላንቲክ ውቅያኖስ የገባችበት የጠፋውን ቱሪስቶች መጓጓዥ ጠላቂ ጀልባ ለማግኘት ሰፊ ፍለጋ እየተካሄደ መሆኑ ተሰማ፡፡


ጠላቂዋ ጀልባ ከትናንት በስቲያ አንስቶ ግንኙነቷ መቋረጡን CNN በድረ ገጹ ፅፏል፡፡


ጠላቂዋ ጀልባ ቱሪስቶችን እና ተመራማሪዎችን ታይታኒክ መርከብ ወደ ሰጠመችበት ስፍራ በማጓጓዝ የምትታወቅ ነች ተብሏል፡፡


ግዙፏ መርከብ ታይታኒክ የሰመጠችው ከ111 ዓመታት በፊት እንደሆነ ዘገባው አስታውሷል፡፡


ወደዚያው ቱሪስቶችን እና ተመራማሪዎችን የምታጓጉዘው ጠላቂ ጀልባ 5 ሰዎችን እንዳሳፈረች ነው የገባችበት የጠፋው፡፡


የቀራት የእስትንፋስ መደገፊያ /ኦክስጂን/ ከ4 ቀናት ያልበለጠ በመሆኑ ፍለጋው ከጊዜም ጋር እሽቅድምደፍም ውስጥ የተገባበት ነው ተብሏል፡፡


ባሕር ጠላቂ መርከቦች ፣ አውሮፕላኖች እና ሄሌኮፕተሮች የተሰለፉበት ታላቅ የነፍስ አድን ጥረት እየተደረገ መሆኑን የካናዳ እና የአሜሪካ የባህር ሀይል ሹሞች ተናግረዋል፡፡



የኔነህ ከበደ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

https://bit.ly/33KMCqz

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page