ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ባለፉት ሁለት ዓመታት በዋግኽምራ ዞን በድርቅ ለተጎዱ እና ለተፈናቃዮች ሲያቀርቡ የነበረው አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ በዚህ ዓመት በ65 በመቶ ቀንሷል ተባለ፡፡
ይህ መሆኑ ደግሞ ድርቅ እየፈተነው ያለውን የህብረተሰብ ክፍል አቅም እያሳጣው ነው ተብሏል፡፡
ይህንን ያለው የዋግህምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋትና ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት የአስራ አንድ ወራቱን ግምገማ ሲናገረ ነው፡፡
ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ያለው የዞኑ ችግር ተገምግሟል ያሉት የፅህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ምህረት መላኩ በጦርነት ምክንያት ቀያቸውን ለቀው ለነበሩ እና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው የዞኑ ነዋሪዎች ሲደረግ ከየነበረው ድጋፍ ቀንሶ 35 በመቶ ሆኗል ብለዋል፡፡
Comments