top of page

ታህሣስ 2፣2017 - ወርልድ ቪዥን በሶስት ክልሎች ለሰላም ግንባታ የ2 ሚሊዮን ዩሮ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ፡፡

ወርልድ ቪዥን በሶስት ክልሎች ለሰላም ግንባታ የ2 ሚሊዮን ዩሮ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ፡፡


ፕሮጀክቱ በግጭት ውስጥ በነበሩና ላሉ ሶስት ክልሎች ላይ የሚተገበር ነው ተብሏል፡፡


የትግራይ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና የአማራ ክልሎች ፕሮጀክቱ የሚተገበርባቸው ናቸው ተብሏል፡፡


በሰላም ግንባታ ፕሮጀክቱ ወጣቶችና የሃይማኖት አባቶች ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል፡፡


ችግሮችን በንግግር የመፍታት ባህልን ማዳበር፣ መተማመን እንዲበረታ መስራት፣ ማህበራዊ ትስስርን ከፍ ማድረግና ውጥረቶችን መቀነስ የፕሮጀክቱ ዋና አላማ መሆኑን ሰምተናል፡፡


ለሰላም ግንባታ ፕሮጀክቱ በሶስቱ ክልሎች በሚገኙ 12 ወረዳዎች ተፈፃሚ ይሆናል ተብሏል፡፡


በዚህም 33,000 ሰዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል፡፡


ሁለት ሚሊዮን ዩሮ በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ የተገኘ ሲሆን የሚያስፈፅመው ደግሞ ወርልድ ቪዥን ነው ተብሏል፡፡


ፕሮጀክቱ በ18 ወራት ውስጥ ይተገበራል፡፡


በፕሮግራሙ ማክበሪያ መርሃ ግብር ላይ የወርልድ ቪዥን የአውሮፓ ህብረት እንዲሁም የክልልና የፌዴራል የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q


📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


bottom of page