ታህሳስ 11፣2017 - አማራ ባንክ "አባ QR Code " በሚል ስያሜ ያዘጋጀውን መተግበሪያ አገልግሎት አስጀመረ
- sheger1021fm
- Dec 20, 2024
- 1 min read
አማራ ባንክ "አባ QR Code " በሚል ስያሜ ያዘጋጀውን መተግበሪያ አገልግሎት አስጀመረ።
መተግበሪያው ተገልጋዮች ማንኛውንም አይነት ግብይት ሲፈጽሙ የእጅ ስልካቸውን ብቻ በመጠቀም በየግብይት ማዕከሉ የሚገኘውን የነጋዴውን QR Code ያለ ጥሬ ገንዘብ ከማንኛውም የባንክ ሂሳባቸው ወይም የሞባይል ባንክ መተግበሪያ ክፍያ መፈፀም የሚችሉበት መሆኑ ተነግሯል።
በአባ ኪው አር ደንበኞች ለግብይት ወይም ለተጠቀሙት አገልግሎት ለነጋዴው የተዘጋጀውን የፈጣን ምላሽ አሻራ በእጅ ስልካቸው ቅኝት ሲያደርጉ ወዲያውኑ የገዙትን እቃ ወይም አገልግሎት አይነት፣ ዝርዝር፣ ብዛት እንዲሁም ዋጋ በስልካቸው ማየት እንዲችሉ ያደርጋል ሲሉ የባንኩ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዩሀንስ አያሌው(ዶ/ር) ተናግረዋል።
ነጋዴዎች ደግሞ በአማራ ባንክ ፈጣን ምላሽ መተግበሪያ አማካኝነት ምርትና አገልግሎታቸውን የዋጋ ማሻሻያ፣ ተጨማሪ የአቅርቦት ዝርዝር ወይም ሌሎች አገልግሎቶችን ለማካተት ቢፈልጉ በማንኛውም ጊዜ ማስተካከያ ማድረግ ይችላሉ ተብሎለታል።

#አማራ_ባንክ ትናንት ወደ ስራ ያስገባውን ጨምሮ ሌሎች የዲጅታል የባንክ አገልግሎት ለደንበኞች ለማድረስ እየሰራ መሆኑን የተናገሩት ዋና ስራ አስፈፃሚው በቅርቡም የዲጅታል ብድር አገልግሎ ተጠቃሽ ነው ብለዋል።
የባንኩ ሞባይል መተግበሪያ ደንበኞች ክፍያን መፈፀም፣ ገንዘብ ማስተላለፍ፣ የአየር ትኬት መቁረጥ፣ የውሃ ክፍያ መፈፀምን ጨምሮ ደንበኞች ግብር የሚከፍሉበትን ስርዓት አቅርቤያለሁ ብሏል።
ባንኩ የዲጅታል ባንክ አገልግሎትን የበለጠ ለማስፋት ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከሳፋሪኮም፣ ከብሔራዊ ስዊች፣ ከፋይናንስ ቴክኖሎጂ አቅራቢዎች፣ ከክፍያ አመቻቾች እና እንደ ገቢዎች ሚኒስቴር ካሉ መንግስታዊ ተቋማት ጋር እየሰራሁ ነው ብሏል።
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://t.ly/9uH-g
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentarios