በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በሚያጋጥሙ የፀጥታ ችግሮች፣ ግጭቶች እና ጥቃቶች ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያው ተጠልለው ዓመታትን ያስቆጠሩ ሚሊዮኖች ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ተቀብላ ባፀደቀቺው የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን አያያዝና መብት የሚመለከተው የካምፓላው ስምምነት ተፈናቃዮች በ6ወር ውስጥ ተመልሰው መቋቋም እንዳለባቸው ይደነግጋል፡፡
በተጨማሪም መልሰው ሲቋቋሙ የተፈናቃዮቹን ሀሳብ ሊከበር እንደሚገባም እንዲሁ፡፡
ይሁንና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተፈናቀሉባቸው አካባቢዎች የሰላም ሁኔታ ሳይረጋገጥ በግዴታ ወደ ነበራችሁበት ካልተመለሳችሁ የዕለት እርዳታ አታገኙም የሚል ግፊት በርትቶብናል የሚሉ ተፈናቃዮች እየበዙ ነው፡፡
በጉዳዩ ላይ በደብረ ብርሃን የተጠለሉ የ40,000 ስደተኞች ተወካዮቻቸውን ጠይቀናል፡፡
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Comments