top of page

ታህሳስ 22፣2017 - የሽግግር ፍትህ ፖሊሲ ተግባራዊ ሲደረግ ይገጥማሉ ተብለው የሚታሰቡ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ምንድናቸው?

በኢትዮጵያ ለዓመታት የተፈፀሙ በደሎች ተጣርተው፣ በዳዮችን በህግ ለመጠየቅ፣ ተበዳዮችም ለመካስ፣ እርቅና ይቅርታን ለማውረድ #የሽግግር_ፍትህ ያስፈልጋል በሚል ወደ ስራ ተገብቷል፡፡


ለዚህም በባለሞያዎች ተመክሮበት የተረቀቀና በኢትዮጵያ ለመተግበር ያመቻል የተባለ ፖሊሲም ወጥቶ በእንደራሴዎች ምክር ቤት በሚያዝያ ወር 2016 ዓ.ም ፀድቋል፡፡


የሽግግር ፍትህን ተግባራዊ በማድረጉ ይረዳሉ የተባሉ 4 ተቋማት በ #አዋጅ መቋቋም እንደሚኖርባቸውም በረቀቀው ፖሊሲ ላይ ሰፍሯል፡፡

የእነዚህ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጆችም በእንደራሴዎች በቅርቡ ይጸድቃሉ መባሉንም ሰምተናል፡፡


ለመሆኑ አሁን በኢትዮጵያ ያለው ነባራዊ ሁኔታ የሽግግር ፍትህን ለመተግበር ያመቻል ወይ?


ፖሊሲው ተግባራዊ ሲደረግስ ይገጥማሉ ተብለው የሚታሰቡ #ችግሮችና መፍትሄዎቻቸውስ ምንድናቸው?


የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን ካረቀቁት ባለሞያዎች መካከል እንዱ የነበሩትን ማርሸት ታደስ (ዶ/ር)ን ጠይቀናል፡፡


ማርሸት ታደስ (ዶ/ር) ለፖሊሲ ትግበራው ይረዳሉ በተባሉ ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጆች ላይ ከሌሎች ባለሞያዎች ጋር እየሰሩም ይገኛሉ፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በማርታ በቀለ

Comments


bottom of page