የጋሞ ዞን አስተዳደር ‘’ኢሰመኮ ትናንት ያወጣውን መግለጫ አልቀበለውም’’ አለ፡፡
በጋሞ ዞን አርባ ምርጭ ዙሪያ ወረዳ ውጥረት ተከስቶ የነዋሪዎች ሰብአዊ መብት እየተጣሰ እንደሆነና ለዚህም አስቸኳይ ምላሽ እንደሚሻ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ትናንት ባወጣው መግለጫ ጠይቋል፡፡
ኢሰመኮ በመግለጫው በአካባቢው በተከሰተው ውጥረት የሰው ሕይወት መጥፋትን ጨምሮ ሌሎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተፈፅመዋል ማለቱን መዘገባችን ይታወቃል፡፡
ሸገር ከአካባቢው ተፈጥሮአል ስለተባለው ውጥረትና እየደረሰ ነው ስለተባለው የሰብአዊ መብት ጥሰት የዞኑ አስተዳደርን ጠይቋል፡፡
የጋሞ ዞን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አባይነህ አበራ ኢሰመኮ ያወጣው ሪፖርት መሰረት የሌለውና በመረጃ ያልተደገፈ ሲሉ ጠርተውታል፡፡
ዞኑ በአሁኑ ሰዓት ሰላም ነው ያሉት ምክትል ዋና አስተዳዳሪው ‘’ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ መንግስት ህግ በሚያስከብርበት ወቅት ሸሽተው ወደ ጋሞ ዞን የገቡ አሉ’’ እነሱንም ቢሆን ክትትል እየተደረገባቸው ነው ብለውናል፡፡
ኢሰመኮ ባወጣው መግለጫ የተፈጠረው ውጥረትን በተመለከተ ከአካባቢው አስተዳደርና የፀጥታ አካላት ጋር ውይይት ሳደርግ ቆይቻለሁ ቢልም የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ በበኩላቸው ኢሰመኮም ሆነ ማንኛውም የሰብአዊ መብት ተቋም መረጃን ሲያጣራ የዞኑ አስተዳደር ማነጋገር ይገባዋል፤ እስካሁን ድረስ ግን ኢሰመኮም ሆነ ሌላ አካል የጠየቀንም ሆነ ያነጋገረን የለም ብለዋል፡፡
ለመሆኑ በጋሞ ዞን በአርባ ምንጭ ዞሪያ በልዩ ወረዳ እንዋቀር የሚሉ ነዋሪዎች የሉም ወይ ብለን የጠየቅናቸው አቶ አባይነህ ያሉት ተከታዩን ነው፡፡
ማንያዘዋል ጌታሁን ያሰናዳውን በንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ… https://bit.ly/33KMCqz
Commentaires