አካል ጉዳተኞችን በተመለከተ ሊጠበቁላቸው ከሚገቡ መብቶቻቸው ውስጥ በሁሉም አገልግሎቶችና ስራዎች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ ሊሰራበት ይገባል ተባለ፡፡
በተለይ አካል ጉዳተኞች በጥበብ ስራዎች ላይ የሚከውኗቸው ስራዎች የላቁ ቢሆኑም ተመልካች አገኝተው ወደ እውቅና ዘርፍ የሚመጡት ጥቂቶችን እንደሆኑ ተነግሯል፡፡
ዓለም አቀፉን የአካል ጉዳተኞች ቀን አስመልክቶ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና ከዓለም ጋለሪ ጋር በመተባበር በተሰናዳ ኤግዚቢሽን የአካል ጉዳተኞችን መብቶች ማስከበር ላይ የተከወኑ ካሉ ስራዎች በአካል ጉዳተኞች የሚሰናዱ የጥበብ ስራዎችን መደገፍ አንዱ እንደሆነ ተነግሯል፡፡
በኢግዚቢሽኑ ላይ በተለያየ የሙያ መስክ የተሰማሩና አካል ጉዳተኛ የሆኑ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ሲሆን ስለ ጥበብ ስራዎቻቸውም ነግረውናል፡፡
በኤግዚቢሽኑ ላይ የቀረቡት የስዕል ስራዎች አካል ጉዳተኞች የሚገጥሟቸው የተለያዩ ፈተናዎች እንዲሁም ተስፋዎች ያንፀባረቁበት ነው፡፡
60 አካል ጉዳተኞች የስዕል ስራዎቻቸውን ያቀረቡ ሲሆን በኢግዚቢሽኑ ከተሳተፉት መካከል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች ህፃናት አካል ጉዳተኞችና አረጋዊያን መብቶች ኮሚሽነር የሆኑት ርግብ ሐዋሪያ አንዷ ናቸው፡፡
የአካል ጉዳተኞች መብቶችን በተለይ ደግሞ አካል ጉዳተኞች በተለያዩ ዘርፎች የሚያጋጥሟቸውን መሰናክሎች የሚያሳዩ ብዙ ስዕሎች አሉ፡፡ በስራውም ተሳትፌአለሁ ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዓለማቀፉን የአካል ጉዳተኞች ቀን አስመልክቶ በተሰናደው የስዕል ኤግዚቢሽን የተለያየ የአካል ጉዳት ያለባቸውና በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሙያዎች የተካፈሉበት ሲሆን እስከ ጥር 6 2017 ዓ.ም እንደሚዘልቅና ለጎብኚዎቹም ክፍት መሆኑን ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/2brw7n5u
ምህረት ስዩም
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs
Comments