ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ማሻሽያ ካደረገች ስድስት ወር ሞላት፡፡
ያለፉት ስድስት ወራት ለኢትዮጵያ ባንኮችን ስኬት ወይስ እንቅፋት? የውጭ ምንዛሪ ማሻሽያው በባንኮች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ ምንድነው?
በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንቲትዩት የባንክ እና ፋይናንስ ተመራማሪ የሆኑት የተወልደ ግርማ(ዶ/ር) ጥናት ለእነዚህ ጥያቄ መልስ ይሰጣል፡፡
ተወልደ ግርማ የውጭ ምንዛሪ ገበያ መር እንዲሆን ሲወሰን ሁሌም ቢሆን በባንኮች ላይ ከፍተኛ ጫና እንደሚሳድር ነግረውናል፡፡
በውጭ ገንዘብ ተበድረው የነበሩ ባንኮች ከማሻሽያው በፊት ይከፍሉት የነበረውን እዳ በሁለት እና በሶስት እጥፍ ከማሻሽያው በኋላ እንዲከፍሉ አድርጓል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ማሻሽያው በባንኮች የማይመለስ ብድር ላይም ከፍተኛ ጫና ማሳደሩንም ተመራማሪው በጥናታቸው ተመልክቻለው ይላሉ፡፡
በዚህም በውጭ ገንዘብ የተወሰዱ ብድሮች እስካሁን በሚፈለገው ደረጃ ለባንኮች እንዳልተመለሰም ዶ/ር ተወልደ ግርማ አስረድተዋል፡፡
ተመራማሪው፤ የውጭ ምንዛሪ ማሻሽያው የሀገሪቱ ባንኮች የባህሪይ ለውጥ እንዲደርጉ ማስገደዱንም አስረድተዋል፡፡
ለምሳሌም ባንኮች የውጭ ሀገር ገንዘቦችን ዋጋ በመመልከት የብድር አሰጣጣቸውን ወደ ውጭ ለሚላኩ ምርቶች እንዲያዘነብሉ አድርጓል ብለዋል፡፡
ሌላው የባህሪይ ለውጥ ከማሻሽያው ወዲህ ዜጎች የሀገራቸው ገንዘብ የመግዛት አቅሙ በመዳከሙ ምክንያት በባንክ ያላቸውን ገንዘብ ወደ ውጭ ምንዛሪ እንዲለውጡ እና እንዲስቀምጡ አድርጓል ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንቲትዩት የባንክ እና ፋይናንስ ተመራማሪ የሆኑት ተወልደ ግርማ(ዶ/ር) ከማሻሽያው በፊት ያልነበሩ ሶስት አዳዲስ ለውጦች መኖራቸውን በጥናታቸው ለይተናል ይላሉ፡፡
እነሱም ከዚህ በፊት ያልነበሩ ማለትም በባንኮች መካከል ያለው ውጭ ምንዛሪ ግብይት ጭምሯል፣ የሀገሪቱ ገንዘብ ክምችት ጭማሪ እና የውጪ ምንዛሪ ቢሮዎች መከፈት ናቸው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
አሁን አገሪቱ ባንኮች ላለባቸው ተጽዕኖ መውጫ መንገድ ይሆናል ያሉንት ምክረ ሀሳቡም ነግረውናል፡፡
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs
コメント