top of page

ታህሳስ 25፣2017 - በሶማሊያ የተሰማራው የአፍሪካ ህብረት የድጋፍና ማረጋጋት ተልዕኮ (AUSSOM) ውጤታማ እንዲሆን ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ተስማሙ

በሶማሊያ የተሰማራው የአፍሪካ ህብረት የድጋፍና ማረጋጋት ተልዕኮ (AUSSOM) ውጤታማ እንዲሆን ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ተስማሙ፡፡


የAUSSOM ተልዕኮ ውጤታማ እንዲሆን ሁለቱ ሀገራት ከስምምነት ላይ የደረሱት በመከላከያ ሚኒስትሯ አይሻ መሀመድ የተመራ የልዕክ ቡድን በሶማሊያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ባደረገበት ወቅት መሆኑንን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡


ሚኒስትር አይሻ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለሶማሊያው ፕሬዘዳንት ሀሰን ሼክ መሐሙድ የተላከን መልዕክት ማድረሳቸውና ከፕሬዘዳንቱም ጋር ውጤታማ የሆነ ውይይት ማድረጉ ተነግሯል፡፡


ውይይቱም ሁለቱ ሀገራት በሶማሊያና በቀጠናው ሰላምና መረጋጋት እንዲረጋገጥ በጋራ ለመስራት ያላቸው ቁርጠኝነት ያደሱበት ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ አስረድቷል፡፡

ሁለቱ ሀገራት ውይይትና ጉብኝት ለማጠናከር ተስማምተዋል የተባለ ሲሆን በዚህም የሶማሊያ ከፍተኛ ባለስልጣናት በቅርቡ በአዲስ አበባ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ሲል መግለጫው ተናግሯል፡፡


የሶማሊያው የመከላከያ ሚኒስትር አብዱልቃድር መሐመድ ኑር ጃም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በሶማሊያ ሰላም እንዲመጣ የከፈለውን መስዋዕትነትና ላበረከተው አስተዋጽኦ አክብሮና ምስጋና ማቅረባቸውም ተሰምቷል፡፡


ኢትዮጵያ የሶማሊያን ሉአላዊነት ባከበረ መልኩ የባህር በር የማግኘት ፍላጎቷን እንድታሳካ የሚያስችላትን ስምምነት በቱርክ አሸማጋይነት ከሶማሊያ ጋር ከተፈራረመች ወዲህ የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲዊ ግንኙነት ሞቅ ሞቅ እያለ ይመስላል፡፡


ከሳምንት በፊትም በሶማሊያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ አሊ ሞሐመድ ኡመር የተመራ የልዑክ ቡድን በኢትዮጵያ ጉብኝት ማድረጉ ይታወሳል፡፡


የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተካተቱበትና በመከላከያ ሚኒስትሯ አይሻ መሐመድ የተመራው የልዑክ ቡድን የሶማሊያ ጉብኝት ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ ሁለቱ ሀገራት በ AUSSOM ተልዕኮ መሳካት በትብብር እንደሚሰሩ መስማማታቸው ከመግለፅ ባለፈው የኢትዮጵያ ተሳትፎ በተመለከተ ያለው ነገር የለም፡፡


ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ግንኙነት በደፈረሰበት ወቅት ከትላንት በስቲያ ጀምሮ በተሰመራው የአውሶም ተልዕኮ ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች እንዲሳተፉ ሶማሊያ እንደማትፈልግ በተደጋጋሚ መናገሯ ይታወሳል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


留言


bottom of page