top of page

ታህሳስ 26፣2017 - የእንጀራ ልጁን ከ10 ዓመቷ ጀምሮ አስገድሮ ሲደፍር የቆየውን ከ10 ዓመት በኋላ እንደገደላት የተረጋገጠበት ግለሰብ ሞት ተፈረደበት

የእንጀራ ልጁን ከ10 ዓመቷ ጀምሮ አስገድሮ ሲደፍር የቆየውን ከ10 ዓመት በኋላ እንደገደላት የተረጋገጠበት አቶ ሚካኤል ሽመልስ ጌታሁን የተባለ ግለሰብ ሞት ተፈረደበት፡፡


በአዲስ አበባ አንዲትን ህፃን ከ10 ዓመት እድሜዋ ጀምሮ ለዓመታት በተደጋጋሚ በመድፈርና በመጨረሻም በመግደል ወንጀል የተከሰከው ግለሰብ ሞት ተፈረደበት፡፡


ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ተከሳሹ የሟች እንጀራ አባት ሲሆን ከ10ኛ አመት እድሜዋ ጀምሮ ለማንም እንዳትናገር በማስፈራራት አስገድዶ የመድፈር ወንጀል ሲፈፅምባት ቆይቷል፡፡


የድርጊቱ ሰለባ የሆነቸው ሟች አዶናዊት ይሄይስ በተከሳሽ የእንጀራ አባቷ እስከተገደለችበት 2015 ዓ.ም ድረስ 2 ጊዜ እንዳስረገዛት እና የመጀመሪያው እድሜዋ 19 አመት እንደሆነ በማስመሰል በሀሰተኛ ማስረጃ ፅንሷን እንድታስወርድ አስገድዷት ነበር ተብሏል፡፡


እንዲሁም በ2015 ዓ.ም መስከረም ወር ላይ ፖሊሶች ይሄን ወንጀሉን በተመለከተ  በደረሳቸው ጥቆማ ሊይዙት ወደ ቤት በመጡ ጊዜ በመስኮት ወጥቶ ካመለጣቸው በኋላ ተመልሶ በእናቷ ፊት ደጋግሞ በቢላ በመውጋት ሲገድላትም በጊዜው የ25 ዓመት የነበረችው ሟች እርጉዝ እንደነበረች ተረጋግጧል ተብሏል፡፡


በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ልዩ ቦታው 15 ሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ተፈፅሟል የተባለውን ይሄንኑ ወንጀል የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ውንብድና ችሎት ክስ ቀርቦበት ሲከራከር ቆይቶ ጥፋተኝነቱም ተረጋግጦበት ችሎቱ ትናንት የሞት ፍርድ እንደፈረደበት ሰምተናል፡፡

Comments


bottom of page