በበዓላት ወቅት የኤሌክትሪክ መቆራረጥ ማጋጠም የተለመደ ሆኖ ቆይቷል፡፡
በበዓላት ወቅት የኤሌክትሪክ ፍላጎት በመጨመሩ የሀይል መቆራረጥ እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል የተባለ ሲሆን ከዚህ ቀደም ባሉት የበአላት ወቅት ሲፈጠር የቆየውን የሀይል መቆራረጥ ለመቀነስ አቅጄ እየሰራሁ ነው ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተናግሯል፡፡
47 ከመቶ የሚሆነው የሀይል መቆራረጥ የሚከሰተው በኤሌክትሪክ ምሰሶዎች እና በመሰረተ ልማቶቹ ዙሪያ በቅርበት የዛፎች መኖር መሆኑን በጥናት ለይቻለሁ ብሏል አገልግሎቱ፡፡
ለሀይል መቆራረጡ ምክንያት የሆነው በመሰረተ ልማቶቹ ዙሪያ በቅርበት የ #ዛፎች መኖር በተለይ ደግሞ በዓላት ሲመጡ ችግሩን ይጨምረዋል ተብሏል፡፡
ይህንን ለማስተካከል ደግሞ የቅድመ ጥገና ስራዎችን ስንሰራ ቆይተናል ያሉት የአገልግሎቱ የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ታዬ የከወነው ስራም በተለይ በበዓላት ወቅት የሚፈጠርን የሀይል መቆራረጥ ይቀንሰዋል ይላሉ፡፡
በተጨማሪም በዋዜማው እና በዕለቱ ከዚህ ቀደም የተለመደው አይነት የሀይል መቆራረጥ እንዳይከሰት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ጋር በመሆን አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አድርጌአለሁ ብሏል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፡፡
ምንአልባትም በዕለቱም ሆነ በ #ዋዜማው የሀይል መቆራረጡ የሚከሰት ከሆነም አስቸኳይ ጥገና ለመስጠት 24 ሰዓት በስራ ላይ ያለ ቡድን አደራጅተናል ይላሉ አቶ መላኩ ታዬ፡፡
በተለይ ደግሞ ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ችግሩ የሚታይባቸው ቦታዎችን በጥናት ለይተን የቅድመ ጥገና ስራ ሰርተን ጨርሰናል ብለዋል፡፡
በእንደዚህ አይነት ጊዜአት የሀይል መቆራረጥ እንዳይፈጠር እና ደንበኞችም እንዳይስተጓጎሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ብቻ የሚሰራው አይደለም ማህበረሰቡም ሊተባበረን ይገባል ብለዋል የተቋሙ የኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ መላኩ ታዬ፡፡
ደንበኞች በበዓላቱ ዋዜማም ሆነ በእለቱ ለሚያጋጥማቸችሁ ችግር፣ ለሚኖራችሁ ቅሬታ እና አስተያየት በ በ904 የጥሪ ማዕከል ደውላችሁ ንገሩኝ ብሏችኋል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
Comments