ኢትዮጵያ ለግብርና ምርቶች የተሰማማ የመሬት ሀብት እና የአየር ጠባይ እንዳላት እየተነገረ ቢቆይም ህዝቧን በበቂ መመገብ አልቻለችም፡፡
የሚበዛው ህዝቧ በገጠር እና በግብርና ኑሮውን የመሰረተ ቢሆንም ዛሬም ከግብረ ሰናይ ድርጅቶች #እርዳታ አልተላቀቀችም፡፡
ሀገሪቱ ለም መሬት፣ ለብዙ ሰብሎች የሚስማማ የአየር ጠባይ፣ ለመስኖ ያመቹ እና ክረምት ከበጋ የሚፈሱ ወንዞች ካላት፣ አምራች የሰው ሀብት ካላነሳት ታዲያ ለምንድነው ህዝቧ በልተው ለማደር የተቸገሩት፡፡
መንግስትስ በህዝቡ #የምግብ_ዋስትና ላይ የሚታይ ለውጥ ማምጣት ለምን ተሳነው?
ጉዳዩን በቀዳሚነት የሚመለከተው የግብርና ሚኒስቴር እና የግብርና ባለሞያን አነጋግረናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…...
ማንያዘዋል ጌታሁን